********
የካቲት ፲፰ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ዓ.ም
“”””””””””””””””””””””””””””
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
******
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ላይ በተከሰተው የቀኖና፣የሃይማኖትና የአስተዳደር ጥሰትን ተከትሎ የተፈጠረውን ወቅታዊ ችግር ምክንያት ጉዳዩን በሽምግልና ለመፍታት የተደራጁት የሽምግልና ኮሚቴዎች (የሀገር ሽማግሌዎች) ችግሩ ከተፈጠረ ወዲህ በኮሚቴው የተሠሩ ሥራዎችን እና ወደፊት ሊሠሩ ስለሚገባቸው ጉዳዩች ለዐቢይ ኮሚቴ፣ለብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ለመንበረ ፓትርያርክ እና ለቅዱስ ሲኖዶስጽሕፈት ቤትዛሬ የካቲት ፲፰ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ዓ.ም ሪፖርቱን አቅርቧል።

በቀረበው ሪፓርት ላይም ሰፊ ውይይት የተደረገበት ሲሆን በሽምግልና ኮሚቴው ወደፊት በሚሰሩ ሥራዎች ዙሪያ ከዐቢይ ኮሚቴው ምክረ ሀሳብ የቀረበ ሲሆን ወደፊትም የቤተክርስቲያን አንድነትና ሉአላዊነት እስከሚረጋገጥና ሁሉም ነገር ወደ ነበረበት ቦታ ተመልሶ መደበኛ አገልግሎታችን እስከሚቀጦል ድረስ የተጣለባቸውን መንፈሳዊ አገልግሎት አጠናክረው እንደሚቀጥሉ፤ በመግለጽ ጉባኤው በጸሎት ተጠናቋል።