መስከረም 1/2017 ዓ.ም
በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በመንበረ ጵጵስና ወናጎ ወረዳ ቤተክህነት ሥር የሚገኘው የዲላ ጎላ ቅዱስ ራጉኤል ቤተክርስቲያን ርዕሰ ዓውደ ዓመት በዓል የሀገረ ስብከታችን የሰበካ ጉባኤ ማደራጃና የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ ክፍል ኃላፊ መልአከ ብርሃን ቀሲስ ዳንኤል ነቢዩ የመንበረ ጵጵስና ወናጎ ወረዳ ቤተክህነት ዋና ፀሐፊ ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ እሸቱ ዋለ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች የዲላና አካባቢው ምዕመናንን በተገኙበት በመንፈሳዊ ክብር ተከብሯል።
በዕለቱም የሀገረ ስብከታችን የሰበካ ጉባኤ ማደራጃና የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ ክፍል ኃላፊ መልአከ ብርሃን ቀሲስ ዳንኤል ነቢዩ የዕለቱን ትምህርት አስተምረዋል። በትምህርታቸውም የቅዱሳን መላእክት ክብርን አማላጅነትን በአዲስ ዓመት አዲስ መንፈሳዊ ሕይወት እንዲኖረን ዘመኑ የሰላም የፍቅር የአንድነት እንዲሆን ሁሉም ክርስቲያን እንደ እግዚአብሔር ቃልና ሀሳብ እንዲኖር ያስተማሩ ሲሆን በአዲሱ ዓመት አዲስ ሰው ልንሆን ይገባናል ብለዋል።
ለዲላ ጎላ ቅዱስ ራጉኤል ቤተክርስቲያን የልማት ሥራ የገቢ የማሰባሰብ ሥራ ተከናውኗል። ሕዝበ ክርስቲያኑ ለቤተክርስቲያን የልማት ሥራ ተሳትፎ አድርጎ ከቅዳሴ በኋላ የበዓሉ ፍጻሜ ሆኗል።