ጥር 15 ቀን 2016 ዓ.ም
“””””””””””””””””””””””
ጋምቤላ-ኢትዮጵያ
””””””””””””””’
ከበዓለ ጥምቀት ማለትም ከጥር 10 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ሲከናወን የሰነበተው የስብከተ ወንጌልና የመዝሙር አገልግሎት በደመቀ ዝግጅት ተጠናቋል።

የተለያዩ መምህራነ ወንጌልና ዘማርያን በጉባኤው ላይ አገልግሎት ሲሰጡ፣ ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል መልእክት እና ቡራኬ ሲያስተላልፉ የሰነበቱ ሲሆን፣ በማጠነቀቂያው ዕለት ጥር አሥራ አራት ቀን 2016 ዓ.ም በርካታ ብፁዓን አበው ነቃ ጳጳሳት ከአዲስ አበባ በመምጣት በጉባኤው ተሣትፈዋል።
በጉባኤው ላይ የተገኙት ብፁዕ አቡነ ማርቆስ፣ በጠቅላይ ቤተ ክህነት የስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ የበላይ ሓላፊ ሊቀ ጳጳስ፣ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ፣ የጉራጌ፣ የምሥራቅ ጉራጌ አህጉረ ስብከትና የቅዱስ ዜና ማርቆስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ሓላፊ ሊቀ ጳጳስ፣ብፁዕ አቡነ ገብርኤል፣ የምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ጳጳስ፣ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም፣ የቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት ጳጳስ፣ ሲሆኑ በጉባኤ ላይ በልዩ ልዩ ርእሰ ወንጌል ቅዱስ ትምህርት ሰጥተዋል።

በጉባኤ ላይ በርካታ ምእመናን የታደሙ ሲሆን፣ የስብከተ ወንጌሉ መርሐ ግብር በብፁዕ አቡነ ማርቆስ ቃለ ምዕዳን እና ቡራኬ ተጠናቋል።

በመጨረሻም፦ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ በጋምቤላ እየተከናወነ ባለው መንፈሳዊ እና ልማታዊ ሥራዎች መደነቃቸውን ገልጸው ለብፁዕ አቡነ ሩፋኤል፣ ለሀገረ ስብከቱ ሠራተኞች፣ ለመላው ሕዝበ ክርስቲያን እና ለክልሉ መንግሥት ምስጋና አቅርበዋል።
©Eotc tv