ጥር 14 ቀን 2016 ዓ.ም ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ፣ በጠቅላይ ቤተ ክህነት የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ የበላይ ሓላፊ ሊቀ ጳጳስ፣ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ፣ የጉራጌ፣ የምሥራቅ ጉራጌ አህጉረ ስብከት እና የቅዱስ ዜና ማርቆስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ሓላፊ ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል የምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም የቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት ጳጳስ፣ ተገኝተው ሕዝበ ክርስቲያኑን እየባረኩ ታቦታቱን ያጀቡ ሲሆን በየማረፊያ በታው ምሕላ በማድረስ ቃለ ምዕዳን ተሰጥተዋል።
በመጨረሻም፦ በፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ ታቦታቱን ወደ መንበረ ክብራቸው በማስገባት የዕለቱ ጉዞ መርሐ ግብር ተጠናቋል።
©Eotc tv