ቤተክርስቲያን ያወጀችውን አዋጅ ተከትሎ ሃይማኖታዊ ተልእኳቸውን በመፈጸማቸው ከሥራ የተባረሩ፣የታሰሩና የተንገላቱ ኦርቶዶክሳዊያን ሪፖርት እንዲያደርጉ የተላለፈ ጥሪ፤

ቤተክርስቲያን ያወጀችውን አዋጅ ተከትሎ ሃይማኖታዊ
ተልእኳቸውን በመፈጸማቸው ከሥራ የተባረሩ፣የታሰሩና የተንገላቱ ኦርቶዶክሳዊያን ሪፖርት እንዲያደርጉ የተላለፈ ጥሪ፤
*********
የካቲት ፲፰ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም
“””””””””””””””””””””””””””
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
******

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅደስ አሐደ አምላክ
አሜን

በኢትዮጵያ ኦርቶድክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በተፈጸመው ሃይማኖታዊ፤ ቀኖናዊ እና አስተዳደራዊ ሕገ ወጥ የኤጴስ ቆጰሳት ሢመት ጋር በተያያዘ በተፈጠሩት ችግሮች እንዱሁም ችግሮቹን መነሻ በማድረግ ቅዱስ ሲኖድስ ጾመ ነነዌን ምክንያት በማድረግ በጾም እና በምህላ አዋጁ መነሻነት ምእመናን ሰማእትነትን ከፍለዋል፤ ከባድ እና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፤ ያለአግባብም ታስረዋል፤ በሕገወጥ መንገድ ተንከራተዋል፤ ተገቢ ያልሆነ ዋጋ ከፍለዋል፤ እንዲሁም ከደመወዝ እና ከሥራ ገበታቸው ጭምር ታግደዋል፤ ተሰናብተዋልም፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ ቅደስ ሲኖዶስ በቤተ ክርስቲያናችን እና በምእመናን ላይ እየደረሱ ያሉ ጥቃቶች እና ጉዳቶች እንዱሁም ሕገ ወጥ ተግባራትን በመከታተል ተገቢውን ሕጋዊ ምላሽ መስጠት የሚችል የሕግ ባለሙያዎች አማካሪ እና ድጋፍ ሰጭ ኮሚቴ በማዋቀር ወደ ሥራ እንዲገባ ተደርጎ ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶችን እያከናወነ ይገኛል፡፡

ስሆነም የደረሱትን እና እየደረሱ ያለትን ጉዳቶች በተመለከተ ተጨባጭ መረጃ እና ማስረጃ ማሰባሰቡ ለነገ የማይባል ተግባር በመሆኑ እና አሁንም የሕግ ክፍሉ በተለያየ መንገድ በሚደርሰው መረጃ ላይ ብቻ ተመስርቶ በውስንነት ድጋፍ እየሰጠ የሚገኝ ስለሆነ መረጃ እና ማስረጃ ያላቸው ማናቸውም ምእመናን እና ምእመናት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ እጆቻችሁ ላይ ያሉ የሰነድ፤የድምጽ፤ እና የምስል ማስረጃዎቻችሁን በሙሉ ከዚህ በታች በተቀመጡት አማራጭ የመረጃ መንገዶች ታሳውቁ ዘንድ የሕግ ክፍሉ ያሳስባል፡፡
በመሆኑም ፦

፩. በማናቸውም የፌዳራል፤ የክልል እና የከተማ መስተዳደር ውስጥ ተቀጥራችሁ ስትሠሩ የነበራችሁ እና ከሃይማኖት ጋር በተያያዘ ከሥራ እና ከደመወዝ የታገዳችሁ እንዱሁም የተሰናበታችሁ በሙሉ ዝርዝር መረጃውን በመላክ እንድታሳውቁን፤

፪. በማናቸውም የፌዳራል፤ የክልል እና የከተማ መስተዳደር ከወቅታዊ ሁኔታ ጋር ተያይዞ በእስር ላይ የሚገኙ ካህናት፤ አገልጋዮች እና ምእመናን ሙለ መረጃ በመላክ እንድታሳውቁን፤

፫. በማናቸውም የፌዳራል፤ የክልል እና የከተማ መስተዳደር ከወቅታዊ ሁኔታ ጋር ተያይዞ የሞት እና የአካል ጉዳት የደረሰባቸውን ካህናት፤ አገልጋዮች እና ምእመናን ሙሉ መረጃ በመላክ እንድታሳውቁን፤ እያሳሰብን ያላችሁን ማናቸውም መረጃ እና ማስረጃዎች ይህ ማስታወቂያ ከተነገረበት ከዛሬ የካቲት ፲፰ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ጀምሮ በስልክ ቁጥር +251985585858 በዋትስአፕ፤ በቴሌግራም ወይም በኢሜይል አዴራሻችን፡-eotcer@gmail.com የሞቱትን፤ የተጎደትን፤ የታሠሩትን እና የተሰወሩትን ሰዎች ስም እና የድርጊቱን ውጤት የሚያሳይ ዝርዝር መረጃ ታጋሩን ዘንድ በቤተ ክርስቲያን ስም ጥሪያችንን እናስተላፋለን፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶድክስ ተዋሕዶ
ቤተ ክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
አዲስ አበባ-ኢትዮጵያ