መጋቢት ፳፯ ቀን ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም
===================
ደምቢዶሎ ኢትዮጵያ
*****
ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል የቄለም ወለጋ፣ የጋምቤላ ክልልና ደቡብ ሱዳን፣ የቤ/ጉሙዝ አሶሳ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የሰላምና የልማት አምባሳደር በዛሬው ዕለት በ27/07/2016 በደምቢ ዶሎ ደ/ጸሐይ መድኃኔዓለም ካቴድራል በመገኘት የታደሰውን ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን በመባረክ፣ ቅዳሴ ቤቱን አክብረዋል።
ብፁዕነታቸው በዚሁ ጊዜ ዕለቱን በተመለከተ ሰፊ ትምህርተ ወንጌል በመስጠት አባታዊ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ አስተላልፈዋል።ለቤተ ክርስቲያኑ የልማት ሥራ የሚህን የ100.000 (አንድ መቶ ሽህ) ብር ድጋፍ ከማድረጋቸውም በተጨማሪ ለካቴድራሉ ሰንበት ት/ቤት የደምብ ልብስ ስጦታ አበርክተዋል በተጨማሪም ለቤተ ክርስቲያኑ መንፈሳዊ አገልግሎት የሚሆን ልብሰ ተክህኖም አበርክተዋል።
ከዚህ በተጨማሪም ብፁዕነታቸው ከሁለት ኩንታል በላይ በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ መልዕክት የታተመበት ቲሸርት በበዓሉ ላይ ለተገኙ ምዕመናንና ምዕመናት በስጦታ ማበርከታቸው ታውቋል።
በሌላ በኩል ለአገልጋዮች የሚሆን በአባ ገዳ የተሰራ ሃያ ነጠላ ያበረከቱት ብፁዕነታቸው ባስተላለፉት አባታዊ መልዕክት ሕዝበ ክርስቲያኑ በአሁኑ ወቅት ቤተ ክርስቲያናችን ከውስጥና ከውጭ የገጠማትን ፈተና በሚገባ በመወጣት በእግዝአብሔር አጋዥነት ችግሩን እናልፈዋለንና በርቱ በሐይማኖታችሁ ጽኑ በማለት መልዕክታቸውን አጠቃለዋል።
ብፁዕነታቸው በትላንትናው እለት በ26/07/2016 ዓ.ም ከሌሊቱ አሥራ አንድ ሰዓት ከአዲስ አበባ በ ወደ ቄለም ወለጋ ሀገረ ስብከት ደምቢ ዶሎ በመጓዝ በዳሌ ሰዲ ወረዳ ቤተ ክህነት ጫሞ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን በአቀባበሉ ወቅት ለተሰበሰበው ሕዝበ ክርስቲያን አባታዊ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ መስጠታቸውን፣ ለህንጻ ቤተ ክርስቲያኑ ግንባታ የሚሆን 20.000.00 ብር ድጋፍ ማድረጋቸውን፣ለደብሩ ሰንበት ት/ቤት የሚሆን መሉ የደምብ ልብስ መለገሳቸውን፣ደምቢ ዶሎ ከተማ ሲደርሱም በሀገረ ስብከቱ ሠራተኞችና በከተማው ማህበረ ምዕመናን ደማቅ አቀባበል የተደረገላቸው መሆኑን የሀገረ ስብከቱ ሕዝብ ግንኙነት ክፍል በላከልን ዘገባ ጨምሮ ገልጾልናል።