የካቲት ፲፱ ቀን ፳፻ ፲ወ፮ዓ.ም
++++++++++++++++++
ባህር ዳር -ኢትዮጵያ
******

ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ወና ሥራ አስኪያጅ፣የባህር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በባህር ዳር ሀገረ ስብከት ለአንድ ሺህ አምስት መቶ አገልጋዮች የክህነት ማዕረግ ሰጡ። በተያያዘ ዜናም ብፁዕነታቸው በሀገረ ስብከቱ በልዩ ዲዛይን የሚታነጸውን የጽርሐጺዮን ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያንና የሀገረ ስብከቱን ጽሕፈት ቤት የግንባታ ሥራ አፈጻጸም አብረዋቸው ወደ ባህር ዳር ከተጓዙ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ጋር በመሆን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ ወቅትም፦
➦ብፁዕ አቡነ ማቲዎስ የምሥራቅ፣የሰሜን አፍሪካና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሐደ ቤተክርስቲያን መገናኛ ብዙሃን ድርጅት ሥርጭት ሊቀ ጳጳስ፣
➦ብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ የደቡብ ኦሞ ጂንካ ሀገረ ስብከትና የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩንቨርሲቲ ሊቀ ጳጳስ፣
➦ብፁዕ አቡነ ሰላማ የምዕራብ ጎንደር መተማ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣
➦መ/ሰ ቆሞስ አባ ወ/ኢየሱስ ሰይፉ የጠቅላይ ቤተክህነት የቋሚና ጊዜያዊ ፕሮጀክቶች ዋና መምሪያ ኃላፊ የተገኙ ሲሆን የደብረ ጸሐይ ሽንብጥ ቅዱስ ሚካኤልን ገዳምንም ጎብኝተዋል።

ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳቱ የካቲት ፳፩ ቀን ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም የጽርሐጺዮን ቅድስት ማርያም ቅዳሴ ቤት የተመሰረተበትን በዓል በባህርዳር ጽርሐጺዮን ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን እንደሚያከብሩ ጉብኝቱን በማስመልከት ከወጣው መርሐ ግብር መረዳት ተችሏል።