የካቲት ፬ ቀን ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም
++++++++++++++++++
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
——————-
ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህር ዳር እና ሰሜን ጎጃም አኅጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰዋሰወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ አስተዳደር እና ደቀመዛሙርትን በመጎብኘት አባታዊ ቡራኬ እና የሥራ መመሪያን አስተላልፈዋል፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይ ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኰንን የጠቅላይ ቤተ ክህነት ምክትል ሥራ አስኪያጅ
የኮሌጁ ዋና ዲን ሊቀ ኅሩያን ሰርፀ አበበ የኮሌጁ የአስተዳደር ሠራተኞች እና ደቀ መዛሙርት የዮሐንስ ንስሐ ልጆች በጎ አድራጊ ማኅበርተኞች ተወካዮች እና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መርሐ ግብሩ ተካሒዷል።

በዕለቱ በዮሐንስ የንስሐ ልጆች ማኅበር እና በሌሎችም በጎ አድራጊ አካላት ለኮሌጁ ደቀ መዛሙርት ቅዱሳት መጻሕፍት ፣ አልጋ ፣ ፍራሽ ፣ እና ሌሎችም ቁሳቁሶችን ለኮሌጁ ለግሰዋል።

በጉባኤው ላይ በኮሌጁ መምህራን እና ደቀ መዛሙርትም ቅኔ የቀረበ ሲሆን በኮሌጁ የአስኳላ ተማሪዎችም መዝሙር በማቅረብ ከብፁዕነታቸው አባታዊ ቡራኬ ተቀብለዋል፡፡

©Eotc tv