ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ወደ አገር እንዳይገቡ ተከለከሉ።

ጥር፳፰ ቀን ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም
“””””” “”””””””””””””””””””
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
******

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በአሜሪካ የነበራቸውን ሐዋርያዊ አገልግሎት ጨርሰው ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ እንዳይገቡ መከልከላቸው ተሰምቷል።

ብፁዕነታቸው ከሳምንታት በፊት በቋሚ ሲኖዶስ እውቅና ወደ ሀገረ ስብከታቸው በመሄድ የአጋእዝተ ዓለም ሥላሴ ዓመታዊ በዓል፣ የከተራና የጥምቀት በዓላትን ከመንፈስ ልጆቻቸው ጋር ያከበሩ ሲሆን ለአዳጊ ሕጻናትም ማዕረገ ዲቁና መስጠታቸው ይታወቃል።

ብፁዕነታቸው በአሁኑ ሰዓት ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያው የሚገኙ መሆኑን ጠቅላይ ጽሕፈት ቤቱ
በአየር መንገድ አቀባበል ለማድረግ በተገኘበት ወቅት አረጋግጧል።

ስለህ ብፁዕነታቸው ወደ አሜሪካ ከመመለሳቸው በፊት የሚመለከተው የመንግስት አካል የቤተክርስቲያናችን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊና የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ መሆናቸውን ከግምት ውስጥ በማስገባት ወደ አገር እንዲገቡ እንዲፈቀድላቸው እንዲደርግ ቅድስት ቤተክርስቲያን ጥሪዋን ታስተላልፋለች።