የካቲት ፲፬/፳፻ ፲ወ፮ ዓ/ም
+ + +
የአዲስ አበባ-ኢትዮጵያ
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የካቲት ፲፫/፳፻፲፮ ዓ/ም የዮርዳኖስ መንግሥት የቱሪዝምና የጥንታውያት ቅርሶች ሚንስትር ክቡር ማክራም ሙስጠፋ አብዱልከሪምን በጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ ተቀብለው አነጋግረዋል።

ቅዱስነታቸው በዮርዳኖስ ሀገር ለምትገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የዮርዳኖስ መንግሥት እያደረገ ላለው መልካም ትብብር ምስጋናቸውን አቅርበው በቀጣይም ከቤተ ክርስቲያናችን ጋር ያለው ግንኙነት ተጠናክሮ መቀጠል በሚችልበት ሁኔታ ላይ ከሚኒስትሩ ጋር በጋራ መክረዋል።

ክቡር ሚኒስትሩም በቅዱስነታቸው ስለተደረገላቸው የክብር አቀባበል አመስግነው ቅዱስነታቸው ሀገረ ዮርዳኖስን እንዲጎበኙ ከሀገራቸው መንግሥት የተላከውን የክብር ጥሪ ማቅረባቸውን የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት አስታውቋል።