ግንቦት ፳፯ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ,ም
“”””””””””””””””””””””””””””

በዓለ ጰራቅሊጦስ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ከብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በአቡዳቢ ደብረ ሰላም መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን በታላቅ ድምቀት ተከብሮ ውሏል።

በቀዓሉ ላይ ለምእመናን ሰፊ ትምህርተ ወንጌል ቃለምዕዳንና ቃለ ቡራኬ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የተሰጠ ሲሆን የአቡዳቢ መድኃኔዓለሕ ቤተክርስቲያን በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ ዲሜጥሮስ ጥያቄ አቅራቢነት በቅዱስነታቸው መልካም ፈቃድ ከዛሬ ግንቦት ፳፯ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ዓ,ም ጀምሮ ምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም ተብሎ እንዲጠራ መሰየሙን መልአከ ሰላም አባ ኪሮስ ወልደአብ በላኩልን ዜና ገልጸዋል።