ሐምሌ ፲፯ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም
“””””””””””””””””””””””””””
ቅዱስነታቸው ከብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትና ከድሬዳዋ ከንቲባ ከአቶ ከድር ጁሀር ጋር በመሆን በድሬዳዋ ከተማ እንዱስትሪ መንደር አዲስ ለሚሰራው የመካነ ሰማእት ቅዱስ እስጢፋኖስ፣ወልደታ ለማርያምና ወአቡነ ሳሙኤል ህንፃ ቤተ ክርስቲያን የመሠረተ ደንጊያ አኑረዋል፣
በተያያዘም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ከብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትና ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ጋር በመሆን የሰበታ ገዳም ቅርንጫፍ በሆነው በድሬዳዋ መልክአ ጀብዱ አቡነ አረጋዊ ሴቶች ገዳም ጉብኝት አድርጓል።
ቅዱስነታቸው ለገዳሙ መነኮሰይያትና በገዳሙ ለሚያድጉ ሕፃናት ሰፊ ትምህርተ ወንጌል መሰጠቱን በመግለጽ ዜናውን ያደረሱን መልአከ ሰላም አባ ኪሮስ ወልደአብ ናቸው።