መጋቢት ፲፪ቀን ፳፻ ፲ወ፭ዓ.ም
****
ባህርዳር -ኢትዮጵያ
“”””””””””””””””””

ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከሚያዝ ፰ -፲፩ ቀን ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም በሀገረ ስብከታቸው ውስጥ ያስጀነመሯቸውን ሕንፃ አብያተ ክርስቲያናትና ልዩልዩፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል ። በፕሮጀክቶቹ ዙሪናም ድጋፍና ክትትልም አድርገዋል፣ ከገዳማትና አድባራት አስተዳደር ክፍሎች ጋርም ውይይት አካሂደው የሥራ መመሪያና ወደፊት መአናወን በሚገባቸው ሥራዎች ዙሪያም አቅጣጫ ሰጥተዋል። ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ከጎበኙዋቸው የልማት ሥራዎች መካከል:-
1.የጽርሐ ጽዮን ገዳም ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን
2. ደብረ መ/አየር ጤና መድኃኔ ዓለም
3.ደብረ አባይ ቅ/ገብርኤል ገዳም
4.ደ/መ/ቅ ከዳነ ምህረት
5.አዲሱ ባሕረ ጥምቀት/40,000 ካሬ መሬት/
6.ቅ/አርሴማ
7. ልደታ ለማርያም
8.የዳጋ እስጢፋኖስ ገዳም ቤተ መዘክር
9. የመንፈሳዊ ኮሌጁን ግንባ ዋና ዋናዎቹ ሲሆኑ ከጉብኝታቸው መልስ የባሕር ዳር ከተማ ዘመን አሻጋሪ ወጣቶች ለቤተ ክርስቲያናቸው መስራት በሚገባቸው የልማት ሥራዎች ዙሪያ ውይይት ያደረጉ ሲሆን ወጣቶቹ ከሀገረ ስብከቱ መመሪያ በመቀበል መሠራት ያለባቸውን የልማት ሥራዎች አጠናክረው እንዲቀጥሉ አባታዊ ምክርና መመሪያ ሰጥተዋል።