ኅዳር ፳፩ ቀን ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም
*******
በየዓመቱ ኅዳር 21 ቀን በከፍተኛ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት የሚከበረውን የኅዳር ጽዮን በዓለ ንግሥ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ_ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ፣ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የልዩ ልዩ የመምሪያ ኃላፊዎች ፣ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና በሽህ የሚቆጠሩ ምእመናን በተገኙበት ዛሬ ኅዳር 21 ቀን 2016 ዓ,ም በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያምገዳም በድምቀት ተከብሯል።
ቅዱስ ፓትርያርኩ ከብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ጋር በመሆን ጧት ጸሎተ ኪዳን አድርሰዋል ፣በመቀጠልም ታቦቱን ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ሥርዓተ ዑደት ከተደረገ በኋላ በገዳሙ ሊቃውንትና ሰንበት ትምህርት ቤት አባላት ወረብ ቀርቧል ፣ በብፁዕ አቡነ ህዝቅኤል ሊቀ ጳጳስ ዕለቱን በተመለከተ ትምህርተ ወንጌል ከተሰጠ በኋላ በመጨረሻ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማናት ሰፊ ትምህርት፣ ቃለ ምእዳንና ቡራኬ ተሰጥቶ የበዓሉ ፍፃሜ ሆነዋል ።