ትንሣኤ ማሳተሚያ ድርጅት
ራእይ
- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በብራና ተጽፈው የሚገኙ ቅዱሳት መጻሕፍት በሙሉ በማሳተሚያ ድርጅቱ በኩል ለኅትመት በቅተው እና ለሕዝበ ክርስቲያኑ ደርሰው ለትምህርትና ለምርምር ያላቸው አስተዋጽኦ ቀጣይነት ያለው ሆኖ ማየት፡፡
ዓላማ
- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊነ፤ህልውት በኩል እንዲትና ቅድስት እንደመሆኗ መጠን ታትመው እንዲሠራጩ የተዘጋጁትን ቅዱሳት መጻሕፍት ሳይበረዙ ና ሳይከለከሉ ይዘታቸውን ጠብቀው ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲሸጋገሩ ማስቻል፡፡
- በበጀት ዓመቱ በቅዱሳት መጻሕፍት ኅትመትና ሥርጭት የሚያስከትለው ሁለንተናዊ ችግር በመፍታት የንባብያን ልምድ ለማሳደግና የአንባብያንን ተደራሽነትና ፋላጎት የበለጠ በማሻሽላል የቤተ ክርስቲያኒቱን ልማት ማፋጠን፤
- ቤተክርስቲያኒቱ ሀገራዊና ዓለም ዓቀፋዊ ድርሻዋን ለመወጣት በምታደርገው ጥረት ማሳተሚያ ድርጅቱ ድርሻውን መወጣት የሚያስችለው ሥራ መሥራት፤
ተልዕኮ፡-
- ቤተ ክርስቲያኒቱ በብራና ተጽፈው ያሉት ቅዱሳት መጻሕፍት እንዳይበላሹ ፣እዳይሠረቁ፣ከማድረግ አንጻር ተጠብቀው እንዲኖሩና ሕዝበ ክርስቲያኑ ለጸሎት፣ ለትምህርትና ለምርምር እንዲጠቀሙባቸው በወረቀት አሳትሞ እንዲሰራጭ ማድረግ፤
- በማሳተሚያ ድርጁቱ የሚታተሙ ቅድሳት መጻሕፍት በተጠነና በተደራጀ መልኩ በተቀመጠለት ጊዜና ሰዓት በተቻለ መጠን ያለምንም እንከን እንዲከናወኑ ማስቻል፡፡
- ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በየደረጃው በመንፈሳዊ አገልግሎቱም ሆነ በማኅበራዊውና በኢኮኖሚው ዘርፍ ሁለንተናዊ አቅም ያላት እንድትሆን ማድረግ፡፡
- ቤተ ክርስቲያኒቱ በማሳተሚያ ድርጅቱ በኩል የምታሳትማቸው ቅዱሳት መጻፍሕትና ልዩ ልዩ ሞዴላ ሞዴሎች በአግባቡና በሥርዓቱ ለሚመለከታቸው አካላት ደርሰው የቤተ ክርስቲያኒቱን ሥርዓትና ተውፊት ሕግና ደንብ ጠብቆ እንዲሰራበትና አገልግሎት እንዲሰጥ ከለማስቻል አንጻር የአገልጋዩና የተገልጋዮና የተገልጋዩ የሥራ ክንውን ውጤታማነትን መፍጠር የሚችል ጥንካሬ ላይ መድረስ ይሆናል፡፡