አስቸኳይ የቅዱስ ሲኖዶስ መልዕክት


አስቸኳይ የቅዱስ ሲኖዶስ መልዕክት፤
“”””””””””””””””””””””””””””””””””
ጥር ፲፯ ቀን ፳፻ ፲ወ ፭ ዓ.ም
*******
አዲስ አበባ -ኢትዮጵያ
“””””””””””””””””””””

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የኒዩወርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በመላው ዓለም ለሚገኙ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳሳት ባስተላሐፉት መልዕክት እንደገለጹት በየትኛውም የዓለማችን ክፍል የሚገኙ አበው ሊቃነ ጳጳሳት በቤተክርስቲያናችን ላይ በተፈጸመው የቀኖና ጥሰትና ህገ ወጥ ድርጊት ዙሪያ ለመወያየት በየትኛውም የዓለማችን ክፍል የሚገኙ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ወደ አገራቸው እንዲገቡ ጥሪ መተላለፉን አስታውሰው በአየር ትራንስፖርቱ ዘርፍ በጉዞአቸው ላይ ችግር እንዳይገጥማቸው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ቅድሚያ እንዲሰጣቸው ከቤቸክርስቲያናችን በቀረቀው ጥሪ መሰረት አየር መንገዱ ፍጹም ፈቃደኛና ተባባሪ መሆኑን አረጋግጧል ብለዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድም የቤተክርስቲያንን ጥሪ ተቀብሎ ፈቃደኛነቱን በመግለጹ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ልባዊ ምስጋናዋን እያቀረበች በየትኛውም የዓለማችን ክፍል የምትገኙ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት አየር መንገዱ የሰጠውን እድል በመጠቀም በደ አገራችሁ በመምጣት ቤተክርስቲያናችን በረጅም ዘመን አገልግሎቷና በታሪኳ ገጥሟት የማያውቀውን ችግር በጋራ ሆነን እንፍታ በማለት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።