መጋቢት ፲፱ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም
*****
አዲስ አበባ-ኢትዮጵያ
“””””””””””””””””””””
ከቤተክርስቲያን በውግዘት የተለዩ 17 የቀድሞ አባቶች ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት በተደረሰው ስምምነት መሰረት 10ሩን የስምምነት ነጥቦች መቀበልላቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ለቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ለብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ዶ/ር አስገብተዋል።
ደብዳቤውን ያስገቡት 17 ሲሆኑ አንዱ ወደ ጸበል መሄዳቸውን ገልጸው ደብዳቤአቸውን በተወካይ አስገብተዋል። በጥቅሉ ደብዳቤ ያስገቡት18 ሲሆኑ ቀሪዎቹ 6 የቀድሞ አባቶች በህመም ምክንያት እንዳልተገኙ በዛሬው ዕለት የተገኙት የቀድሞ አባቶች ገልጸው በቅርብ ጊዜ ቀሪዎቹ ግለሰቦች ማመልከቻቸውን ይዘው እንደሚመጡ ገልጸዋል።