“እኛ ካህናት አስታራቂዎች እንጂ ታራቂዎች መሆን አልነበረብንም፤ በጥሪአችን መሰረት የእውነት ካህናት በመሆን ለቤተክርስቲያን አንድነት መስራት ይኖርብናል፤”
“እኛ ካህናት አስታራቂዎች እንጂ ታራቂዎች መሆን አልነበረብንም፤ በጥሪአችን መሰረት የእውነት ካህናት በመሆን ለቤተክርስቲያን አንድነት መስራት ይኖርብናል፤”
“በቅርቡ በቤተክርስቲያን ላይ ተፈጥሮ የነበረውን ችግር ነገ ላይ ሆነን ስናየው መጸጸታችን አይቀርም፤የዛሬ አመጣጣችሁ የመጨረሻ እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ።”
“በተፈጠረው ችግር ምክንያት በርካታ ምዕመናን ሞተዋል፣የአካልና የሥነ ልቦና ጉዳት ደርሶባቸዋል፣ ታስረዋል፣ከሥራቸው ተፈናቅለዋል፤ስለሆነም ችግሩን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መፍታት አለብን።”
ብፁዕ አቡነ አብርሃም
የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና
የባህርዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
በትላንትናው ዕለት 10ሩን የስምምነት ነጥቦችን እንቀበላለን በማለት የመጡትን 17 የቀድሞ አባቶችን ባነጋገሩበት ጊዜ ካስተላለፉት መልዕክት የተወሰደ፤