ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ
የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የኒዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
(ማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት)
++++++++++++++++++++++++++++++

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የኒዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በማኅበረ ቅዱሳን የ2016 ዓ.ም የ6 ወራት የሥራ አመራር ጠቅላላ ጉባኤ ማጠቃለያ ላይ ተገኝተው ቡራኬና ቃለ ምእዳን ሰጥተዋል።
በዚህ አስፈሪ ጊዜ እግዚአብሔር ሥራ እንድንሠራ ፈቅዷል ያሉት ብፁዕነታቸው በርካታ ችግሮችን አልፋችሁ መጥታችኋል። ዓለም በሚቀማበት ወቅት ጊዜውን፣ገንዘቡን ለቤተ ክርስቲያን የሚሰጥ እንደእናንተ አይነት ልጆች ስላሉን እግዚአብሔርን እናመሰግነዋለን ብለዋል።

ብፁዕነታቸው በመልእክታቸው “የቤተ ክርስቲያን ጥቅም እንጂ ቤተ ክርስቲያን በአእምሯችን የሌለች ሁነናል። እግዚአብሔር ግን በተለያዩ መከራዎች ውስጥ ሁነው ስለሚያለቅሱት ሲል ያሻግረናል፤ራሳቸውን ለመስጠት በተዘጋጁ ምእመናን እናልፈዋለን፤ እነዚህን ከደገፍናቸው ቤተ ክርስቲያን ጸንታ ትኖራለች። እናንተም እነሱን ነው ምታግዙት”ሲሉ ገልፀዋል ።

ከእኛ የሚጠበቀውን በመንፈሳዊነት ከሠራን ሀገር ትለወጣለች፤ ግን አንድ ሁነን፣ በእግዚአብሔር አምነን በጸሎት ሲሆን ነው በማለት አጽዕኖት የሰጡት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ተደማምጠንና ተናበን መሥራት ከቻልን እናልፈዋለን ሲሉ አጽዕኖት ሰጥተዋል።

ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የነበረው የማኅበረ ቅዱሳን ሥራ አመራር ጠቅላላ ጉባኤ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ በማሳለፍና አቅጣጫ በማስቀመጥ ተጠናቋል።