ሚያዝያ ፪ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም
*******
የሆሣዕና በዓል በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተከብሯል።

በተያያዘ ዜና የሆሣዕና በዓል በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት በደብረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያና የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት በድምቀት ተከብሮ ውሏል።

ከዚህ በተጨማሪ በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በባቱ/ዝዋይ ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል ሊቀ ትጉኅን አለቃ ኤርምያስ የአዳሚ ቱሉ ጅዶ ኮምቦልቻ ወረዳ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ ፡ መልአከ ጽዮን ቆሞስ አባ ተክለወልድ መንግሥቴ የካቴድራሉ አስተዳዳሪ በተገኙበት ፡፡ በድምቀት መከበሩን ሐመረ ተዋሕዶ ዘግቧል።

በሌላ ዜና ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል የጋምቤላ፣የቤኒሻንጉል አሶሳ፣ የምዕራብ ወለጋ፣ የቄለም ወለጋና የደቡብ ሱዳን አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በቤተክርስቲያናችን ተከስቶ ከነበረው ችግር በኋላ ለመገመሪያ ጊዜ ጋምቤላ ሀገረ ስብከት የገቡ ሲሆን በክልሉ መንግሥት ከፍተኛ ኃላፊዎች፣በካህናትና በምዕመናን ከፍተኛ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።እስከ ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባም በአምስቱ አህጉረ ስብከታቸው ሐዋርያዊ ጉዞ እንደሚያደርጉ የሀገረ ስብከቱሕዝብ ግንኙነት ክፍል በላከልን ዜና ገልጿል።ብፁዕነታቸው የሆሳዕና በዓልን
በጋምቤላ አቡነ ተክለሀይማኖት ገዳም በታላቅ በድምቀት ማክበራቸውም የደረሰን ዜና ያመለክታል።