መስከረም 16 ቀን 2017 ዓ.ም

ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት የ2017 ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል በወልድያ ከተማ ተከብሯል።

ብፁዕነታቸው እለቱን አስመልክተው ትምህርትና ቃለ ምእዳን ያስተላለፉ ሲሆን ክርስቶስ በመስቀል ተሰቅሎ የከፈለልንን ውድ ዋጋ በመሆኑ ለእውነተኛ ፍቅር እንዲንተጋ አባታዊ መልእክት አስተላልፈዋል።

የወልድያ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት ኀላፊ አቶ ኢትዮጲስ አያሌው የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።

የወልድያ ከተማ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያንና የሰንበት ትምህርት ቤቶች ኅብረት እለቱን የተመለከቱ ወረብና ዝማሬ አቅርበዋል።

መረጃው የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሕዝብ ግንኙነት ክፍል ነው።