የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅሊይ ቤተክነት አስተዳደር ጉባኤ በአዱስ አበባ ሀገረ ስብከት የሚታዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን የሚያጠኑ ፯ አባላት ያሉት ኮሚቴ ሰየመ፡፡

መስከረም ፱ ቀን ፳፻ ፲ወ፯ ዓ.ም
******
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
==============

በሀገረ ስብከቱ የሚስተዋለው ግብረ ሙስና በሚሊየኖች በሚቆጠር ገንዘብ የሚፈጸም መሆኑን በመጥቀስ በዋዜማ ሬዱዮና በሌሎችም የሚዲያ ተቋማት የተዘገበውን ዘገባ በተመለከተ የሀገረ ስብከቱ የህዝብ ግንኙነት ክፍልና የሥራ ኃላፊዎች ጋዜጣዊ መግለጫ በመስጠት ለማስተባበል መሞከራቸው ይታወሳል፡፡

ይሁንና በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ሀገረ ስብከቱ ከቅጥርና ዝውውር ጋር በተያያዘ በሕግና በመመሪያ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ጋር በመናበብ እየሰራ መሆኑን በመግለጽ ያስተላለፈው መግለጫ ፍጹም ሐሰት ከመሆኑም በላይ በተደጋጋሚ በሀገረ ስብከቱ በኩል የሚስተዋለው የመልካም አስተዲደር ችግር በቅዱስ ሲኖዶስ ጸድቆ በተላለፈው መመሪያ መሠረት እንዲፈታና ቅሬታ ለሚያቀርቡ ወገኖችም ይህን መሠረት በማድረግ ፍትሕ እንዱሰጥ በጠቅላይ ቤተክህነት አስተዳደር ጉባኤ ተወስኖ በተደጋጋሚ የተላለፈውን መመሪያ አለመፈጸሙ ጉባኤውን አሳዝኗል።

ስለሆነም በሀገረ ስብከቱ የሚስተዋለው የመልካም አስተዳደር ችግር በፍጹም ቆራጥነትና ተጋድሎ የሚታረምበትና ቤተክርቲያንና አገልጋይ ካህናት እፎይታ የሚያገኙበት ሁኔታ መፍጠር ይቻል ዘንድ ችግሩን በዝርዝር በማጥናት ከመፍትሔ ሐሳብ ጭምር የሚያቀርቡ ፯ (ሰባት) አባላት ያሉት ኮሚቴ እንዱሰየሰሙ አድርጓል፡፡

ችግሩን ለመፍታት የሚደረገው እልህ አስጨራሽ ተጋድሎም ፍጹም ቆራጥነትን የሚጠይቅ በመሆኑ ችግሩ ከስሩ ተፈቶ የቤተክርቲያን ክብር ተመልሶና የካህናት እንባ ታብሶ ቀጣይነት ያለው በህግ የሚመራና የቤተክርስቲያናችንን ቅድስና የሚመጥን አሠራር ተዘርግቶ መፈጸም እስከሚችል ድረስ በቆራጥነት ለመሥራት ጉባኤው በአንድ ድምጽ በመወሰን ዝርዝር ሁኔታውን በማጥናት ከመፍትሔ ሐሳብ ጭምር እንዲያቀርቡ፦

፩. መ/ሰ ቆሞስ አባ ቃለጽድቅ ሙሉጌታ(ዶ/ር) ከጠቅላይ ቤተክህነት፤
፪.ሊቀ መዘምራን ሐረገወይን ጫኔ ከጠቅላይ ቤተክህነት፤
፫.ሊቀ ስዩማን እስክንድር ገብረክርስቶስ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት፤
፬.ዲ/ን ሙሉቀን ትዕዛዙ(ከምዕመናን)
፭.ዲ/ን ዘለዓለም ሲሳይ(ከምዕመናን)
፮.ዲ/ን ዘካርያስ ወዳጆ(ከህግ ቋሚ ኮሚቴ)
፯.ዲ/ን ስንታየሁ ምስጋናውን ከሰንበት ትምህርት
ቤቶች አንድነት በመመደብ የእለቱን ስብሰባ በጸሎት አጠናቋል።