ሰኔ ፳፩ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም
“”””””””””””””””””””””””””
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
******

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት እና ብፁዕ አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት ዛሬ ሰኔ ፳፩ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም የሰኔ ማርያም በዓለ ንግሥ በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በድምቀት ተከበረ ።

ታቦቱ ህጉ በቅዱስነታቸው መሪነት ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ሥርዓተ ዑደት ከተደረገ በኋላ በገዳሙ ሊቃውንትና በሰንበት ት/ቤት ወጣቶች ወረብ ቀርቧል ፣ በብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የሆሣዕና የደቡብ አፍሪካ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ዕለቱን በተመለከተ ትምህርተ ወንጌል ከሰጡ በኋላ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማናት ሰፊ ትምህርት ቃለ ምእዳንና ቡራኬ ተሰጥቶ የበዓሉ ፍፃሜ ሆነዋል ።

በበዓሉ ላይ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት የመምሪያ ኃላፊዎች፣ምዕመናንና ምዕመናት ተገኝተዋል ሲሉ መ/ሰ አባ ኪሮስ ወልደአብ በላኩልን ዘገባ ገልጸዋል።