የቤተክርስቲያናችን የሕግ ባለሙያዎች ኮሚቴ አባል ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ አያሌው ቢታኔ ታሠሩ ።
ታኅሳስ ፱ ቀን ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም
“””””””””””””””””””””””””””
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
ጠበቃ እና የህግ አማካሪ አያሌው ቢታኔ የዕለት ችሎት ተከራርክሮ ከፍርድ ቤት ወጥቶ ከባለቤቱ እና ከእህቱ ጋር ሜክሲኮ በሚገኘው ነዳጅ ማደያ ለመኪናው ነዳጅ በመቅዳት ላይ ሳለ ሲከታተሉት በነበሩ በመንግስት የጸጥታ አካላት ተወስዶ የታሠረ መሆኑ ታወቀ።
ጠበቃ አያሌው ቢታኔ በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት በተቋቋመው የሕግ ባለሙያዎች ኮሚቴን በመምራት ሙያዊ ግዴታቸውን በመወጣት ቤተክርስቲያንን ወክለው የሕግ አገልግሎት ሲያበረክቱ ቆይተዋል። በተለይም በቤተክርስቲያናችን ተከስቶ በነበረው ሕገ ወጥ ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት ተከትሎ ሃይማኖታዊ ግዴታቸውን በመፈጸማቸው በተለያዩ ምክንያቶች ከሥራቸው ለተፈናቀሉ ምእመናን በነጻ የሕግ ማማከርና ጥብቅና አገልግሎት በመሥጠት ከፍተኛ አገልግሎት አበርክተዋል።
በተጨማሪም በቅዱስ ሲኖዶስ በሚወጡ ሕጎችና መመሪያዎችን በማርቀቅ ሰፊ አገልግሎት አበርክተዋል።
© EOTC TV