የካቲት፱ቀን ፳፻ ፲ወ፰ ዓ.ም
++++++++++++++++
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
=============

በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ በተደረገው ሥራና ሠራተኛን የማገናኘት ሥራ ወደ ቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደር ልማት ድርጅት የተመደቡት ክቡር ሊቀ ስዩማን እስክንድር ገብረክርስቶስ በፈጠሩት የአስተዳደር ንድፍ አማካኝነት የተጀመረው ደንበኛ ተኮር የአመራር ስልት መሠረት ሆድና ጀርባ በመሆን ለዘመናት ይኖሩ የነበሩ የድርጅቱን ሠራተኞች ደንበኞች የቤተሰብነት ስሜት መፍጠራቸውን ባለፉት 6 ወራት ውስጥ የተሠሩ ዝርዝር ሥራዎችን፣ እየተሠሩ ያሉና ወደፊት ሊሠሩ የታቀዱ ሥራዎችን የሚገልጽ ሪፖርት ቀርቧል።

ሪፖርቱ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የምስካየ ኅዙናን መድኀኔዓለም ገዳም የበላይ ኀላፊ ፣ ንቡረ ዕድ አልያስ አብርሃ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽሕፈት ቤት በመንፈሳዊ ዘርፍ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ፣ ረ/ፕ ግርማ ባቱ (ቀሲስ) የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽሕፈት ቤት የማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፍ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ፣ ሊቀ መዘምራን ሐረገወይን ጫኔ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽሕፈት ቤት የአስተዳደር መምሪያ ኃላፊ ፣ ሊቀ ስዩማን እስክንድር ገብረ ክርስቶስ የቤቶችና ሕንፃዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅና የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ዋና ኀላፊ ፣ የቤቶችና ሕንፃዎች ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በተገኙበት በድረጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ አማካኝነት ቀርቦ ከድርጅቱ የሥራ ኀላፊዎች ተጨማሪ ሐሳብ ተሰጥቶበታል።

በሪፖርቱ ድርጅቱ ደንበኛ ተኮር ስርዓት ዘርግቶ በሁሉም ሕንፃዎች ላይ የሚገኙ የነዋሪ ተዎካዮች በማቋቋም ሥራ እንዲጀምሩ በማድረግ ከሁሉም ነዋሪዎች ጋር ውይይት በማድረግ ሆድና ጀርባ ሆነው ሲኖሩ የነበሩት የድርጅቱ ደንበኞችና ሠራተኞች ወንድማማችነትን በማጎልበት በየኔነት ስሜት ድርጅቱ በሚያከናውናው የልማት ሥራውዎች ላይ ንቁ ተሳቶፎ እያደረጉ መሆኑ ተገልጿል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ድርጅቱና ነዋሪዎች እንዲሁም መላው የሚመለከተቸው አካላት የሚናቡበት የፌስቡክና የቴሌግራም ገጽ እንዲሁም የነዋሪዎች፣ የድርጅቱ ሠራተኞች የቴሌግራም ምዕላድ በመክፈት የተግባቦት ሥራውን በቀላል መንገድ እንዲካሄድ መደረጉንም የተገለፀ ሲሆን ዓለም አቀፍ ተደራሽነቱን ለማስፋት ድረ-ገጽ መክፈት መቻሉንም አብራርተዋል ድርጅቱ እስከዛሬ በመጣበት የገንዘብና የንብረት አስተዳዳር ስርዓት ወደፊት አንድ ደረጃ መራመድ እንደማይችል በመረዳት የቴክኖሎጂ አገልግሎት ጥቅም ላይ ለማዋል ከባንኮችና ከድርጅቶች ጋር ምክክር እየተደረገ መሆኑም ተገልጿል።

የድርጅቱ ሠራተኞች ሆነው በድርጅቱ ስም የግል ጥቅማቸውን ሲያሳድዱ የነበሩ ግለሰቦች ላይ እርምት በመውሰድ ድርጅቱን ከጥፋት ለመታደግ እንደተቻለና በርካታ ገንዘብ ወጥቶባቸው ተሠርተው የጥራት ጥያቄ የተነሰባቸውን የድረጅቱ ሕንፃዎች ማስተካከያ እንደተረገባቸው ተገልጿል።

ድርጅቱ በጽርሐ ምኒልክ ሕንፃና በተለያዩ የንግድ ቦታዎች ላይ ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የጨረታ ኮሚቴዎች ጋር በመሆን እንዲከራዩ ያደረገ ሲሆን ከካሳ ክፍያዎች ጋር ተያይዞ ከየክፍላተ ከተማ ጋር በመናባብ እየሠራ መሆኑንም ገልጿል።

በተያያዘ ዜና ያልተመለሱ ይዞታዎችን ለማስመለስ ያላሰለሰ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ፣ ለሥራ ኀላፊዎች ቤት የሚያገኙበትን ስርዓት ከመንግሥት የመኖሪያ ቤት አስጣጥን ተመኮሮ በመውሰድ ጥናት ለማቅረብ ጥረት እየተደረገ መሆኑን፣ ሕንፃዎቹ የሚገኙበትን አካባቢ የሚመጥን የቤት ኪራይ ማሻሻያና የቤት ኪራይ ውል አሰጣጥ ማሻሻያ ጥናቶችን አጠናቆ በቅርቡ ለጽሕፈት ቤቱ እንደሚያቀርብና ለቤተክርስቲያን ገቢ የሚያስገኙ ሥራዎችን ለመስራት እቅድ መያዙ ተገልጿል።

በመጨረሻም ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና ምክትል ሥራ አስኪያጆች የቀረበውን ሪፖርት በአድናቆት በመቀበል ለቤተክርስቲያን በመቆርቆር በባለቤትነት ስሜት ለማገዝ ከሚመጣው ይልቅ የራሱን ጥቅም ዓላማው ትችን ስንቁ ያደረገ ሠራተኛ በበዛበት ዘመን በነፍሳችሁ ተወራርዳች ለቤተክርስቲያን ለመስራት ቁርጠኛ ሰለሆናችሁ ከታሪክ ወቀሳ ድናችኋል ብለዋል። የቀረበው ሪፖርት ፈር ቀዳጅና በአጭር ጊዜ ውስጥ ትልቅ አፈፃፀም የታየበት መሆኑን አጽንዖት በመስጠት በዚህ ሥራ ላይ መሪ ተዋናይ የሆኑትን ሁሉ በማመስገን በቀጣይ ጠንክረው እንዲሠሩ አባታዊ መመሪያ ሰጥተዋል።