መስከረም ፲፱ቀን ፳፻ ፲ወ፮ዓ.ም
“””””””””””””””””””””””””””””””
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
“””””””””””””””””””””
በሀሌሉያ ሆስፒታል ሕክምናቸውን ሲከታተሉ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ሰላማ በትላንትናው እለት ከዚህዓለም ድካም ማረፋቸውን ተከትሎ በዛሬው እለት ክቡር አስከሬናቸው ወደበመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ጸልተ ፍትሐት ሲደረግበት እንዲያድር እና በነገው እለት ቅዳሴ ከተቀደሰ በኋላ አስፈላጊው ሥርዓት ከተፈጸመለት በኋላ ሥርዓተ ቀብሩ እንዲፈጸም ወደ መንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ተጉዟል።
በሥነሥርዓቱ ላይ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የኒዩወርክ ሀገረ ስብሰት ሊቀ ጳጳስ፣ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣የጠቅላይ ቤተክህነት መምሪያ ኃላፊዎች፣ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ፣ወዳጅ ዘመዶቻቸው ተገኝተዋል።