የካቲት ፳፭ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም
“”””””””””””””””””””””””””””
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
**
የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ፬ኛ ዓመታ መታሰቢያ በመንበረ ጸባዖት ቅድስ ስላሴ ካቴድራል ብፁዕአን ሊቃነ ጳጳሳት የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት የሥራ ኃላፊዎች፣ የአድባራት አስተዳዳሪዎች ሊቃውተ ቤተክርስቲያን ወዳጆቻቸው እና የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻቸው በተገኙበት በድምቀት ተከብሯል።
ቅዱስ አባታችን የካቲት ፳፬ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም ነው ከዚህ ዓለም ድካም ያረፉት ቅዱስነታቸው በአገር ውስጥ አገልግሎታቸው ቅድስት ቤተክርስቲያንን ማዕከል ያደረጉ በርካታ ሥራዎችን ያከናወኑ፣በንጽሕናና በቅድስና የኖሩ ወደ አገራቸው ከተመለሱ በኋላም በአርምሞና በጸሎት ቅድስት ቤተክርስቲያናችንንና አገራችንን የጠበቁ ታላቅ አባት ነበሩ።