ነሐሴ 10 ቀን 2016 ዓ.ም
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዝዳንትና የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዝዳንት 12ኛ ዓመት የእረፍታቸው መታሰቢያ ክቡር አስከሬናቸው ባረፈበት በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በጸሎተ ፍትሐት ታስቦ ዋለ።

በመርሐ ግብሩ ላይ ብፁእ አቡነ አብርሃም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የባህር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁአ አቡነ ሳዊሮስ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ የሸገር ሲቲ አህጉረ ስብከትና የምስካየኅዘለናን መድኃኔዓለም ገዳም የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ ፣ የጠቅላይ ቤተክህነት የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች እንዲሁም የገዳማትና የአድባራት አስተዳዳሪዎች በርካታ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ካህናትና ምእመናን በተገኙበት ጸሎተ ፍትሐቱ በዛሬው ዕለት ማለትም ነሐሴ 10 ቀን 2016 ዓ/ም ተከናውኖ መርሐ ግብሩ ተጠናቋል።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ለሃያ ዓመታት በፓትርያርክነት ያገለገሉ፣በርካታ መንፈሳዊና ልማታዊ ውጤታማ ሥራዎችን የሰሩ፣ቤተክርስቲያን በዓለም መድረክ ከፍ ብላ እንድትታይ ያደረጉ አባት እንደነበሩ ይታወቃል።