የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት እና የውጭ ግንኙነት መምሪያ ሓላፊዎች ከእስራኤል አምባሳደር ጋር ተወያዩ።

ጥር 26 ቀን 2016 ዓ.ም

+ + +
አዲስ አበባ – ኢትዮጵያ

የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጸሐፊ ክቡር መልአከ ሕይወት ቆሞስ አባ ኃይለገብርኤል ነጋሽ እና የውጭ ግንኙነት መምሪያ ሓላፊ ሊቀ ካህናት ደረጀ መንግሥቱ በኢትዮጵያ ከእስራኤል አምባሳደር ክቡር አለልኝ አድማሱ እና የኤምባሲው ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ተወያይተዋል ።

በውይይታቸውም የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ጽሕፈት ቤት ከኤምባሲው ጋር ያለውን ግንኙነት ማጠናከርን ጨምሮ በጋራ ለመሥራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

በቀጣይም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም አባታዊ መመሪያ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እና በእስራኤል መንግሥት መካከል ያለውን ግንኙነት እና ትብብር ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል።ሲል የቅዱስ ፓትርያርኩ ልዩ ጽሕፈት ቤት በላከልን ዘገባ ገልጿል ።