ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የጉራጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ዻዻስ፣ የቅዱስ ዜና ማርቆስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ኃላፊ፣ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ ቦርድ ሰብሳቢና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ቦርድ ሰብሳቢ በገዳሙ ተገኝተው ቃለ ምዕዳን እና ቃለ በረከት ሰጥተዋል። የጉራጌ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅና የቅዱስ ዜና ማርቆስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ዋና ዲን መጋቤ ስብሃት ሳህሉ ተሰማ፣ በመ/ዽ/ወ/ቤተክህነት የደብረ ብሥራት ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ቆሞስ አባ ገብረ ኢየሱስ አሳዬ በብፁዕነታቸው ተጋብዘው የዕለቱን ቃለ ወንጌል አስተምረዋል።

በእለቱ በቅዱስ ዜና ማርቆስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀ መዛሙርት ያሬዳዊ ዝማሬ ቀርቧል። ገዳሙ እጅግ በርካታ የልማት ሥራዎች እየተሠራበት የሚገኝ ሲሆን እንደ ጉራጌ ሀገረ ስብከትም በርካታ ሊቃውንት ለማፍራት በብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ ሣልሳይ መልካም ፈቃድ እና ክትትል ሰፊ የአብነት ትምህርት ቤት ፕሮጀክት ተቀርጾ እየተሰራበት ይገኛል። በዛሬው እለትም እየተሠሩ ያሉ የልማት ሥራዎች እና የአብነት ትምህርት ቤቶች ጉብኝተ ተደርጓል።

መረጃውን ያደረሰን የሀገሰ ስብከቱ ሕዝቦ ግንኙነት ነው።