በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን የስብክተ ወንጌልና ሀዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ ሊቀ ጳጳስ ብጹእ አቡነ ማርቆስ ጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ በመገኘት ድጋፉን አስረክበዋል፡፡

በደረሰው አደጋ ቤተ-ክርስቲያኗ ማዘኗን የገለጹት አቡነ ማርቆስ፤ ለተጎጂ ወገኖችም መጽናናትን እንደሚመኙ ተናግረዋል፡፡

አሁን እንደተቋም ቤተ-ክርስቲያኗ ካደረገችው ድጋፍ በተጓዳኝ ምዕመኑን በማስተባበርም በቀጣይ ድጋፍ እንደሚደረግም ገልጸዋል፡፡

ድጋፊን የተቀበሉት የጎፋ ዞን ዋና አስተዳደሪ ዳግማዊ አየለ፤ ቤተ-ክርስቲያኗ አደጋው ከደረሰ ጀምሮ ተጎጂዎችን ከማጽናናት ጀምሮ ባደረገችው ያልተቋረጠ ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

በቀጣይ ሌሎች ሀይማኖታዊ ይሁኑ ሀይማኖታዊ ያልሆኑ ተቋማት ተጎጂ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም የሚደረገውን ጥረት እንዲደግፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡