የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ ሥልጠና በመስጠት ላይ ነው።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ ከኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤና ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የስብከተወንጌል እምርታ ለቤተክርስቲያን ከፍታ፣የቤተክርስቲያንን መዋቅር ጠብቆ ማገልል፣የኮረና ቫይረስና ተዛማቾ በሽታዎችን መከላከልን በተመለከተ፣በሽታን መከላከል ከሃይማኖት አስተምህሮ አንጻር በሚሉና ሌሎች ርዕሰ ጉዳዩች ዙሪያ ከጥቅምት ፲፬ -፲፭ ሸን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ/ም በጠቅላይ ቤተክህነቴ ጽርሐ ተዋሕዶ አዳራሽ ለጠቅላይ ቤተክሄነት መምሪያ ኃላፊዎች፣ለአህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆችና የስብከተ ወንጌል ክፍል ኃላፊዎች ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል።
በስልጠና መርሐ ግብሩ መክፈቻ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጠቅላይ ጸሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ ከኮረና ቫይረስ ወረርሽኝ ጋር ተያይዞ ወቅታዊ መረጃዎችና የተግባቦት መንገዶችን በመጠቀም ረገድ የሃይማኖት ተቋማት ሊኖራቸው በሚገባ ሚና ላይ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን በቀጣይ በሌሎች የጋራ እሴቶች ዙሪያ ተመሳሳይ ስልጠናዎች እንደሚሰጥም ገልጸዋል።
በስልጠናው ላይ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ የመምሪያው የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስና ክቡር ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ተገኝተዋል።