የካቲት 09 ቀን 2018 ዓ/ም
ድጋፉ የተደረገው በብፁዕ አቡነ ሳሙኤል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ መሪነት ሲሆን ተማሪዎችን በተለያየ የሞያ ዘርፍ እራሳቸውን ብቁ የሚያደርጉበት ንብረቶች ተበርክቷል
በዕለቱም ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ ፣ መጋቤ ኅሩያን አባ ኤልያስ በልሁ የምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም ዋና አስተዳዳሪ ፣ አቶ ወርቁ አሸናፊ የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር ፣ አቶ ይልቃል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ኮሚሽነር ፣ የገዳሙ ጽ/ ቤት አገልጋዮች በተገኙበት ድጋፉ ተበርክቷል ።
ለተማሪዎች ለትምህርታቸው ይጠቅማል ብለን ያሰብናቸው እቃዎች ዛሬ አስረክበናል በተለያየ አጋጣሚ ይህንን ትምህርት ቤት ጎብኝተናል ትምህርት ቤቱ ቤተክርስቲያን አለችኝ ከምትለው የምንኮራበት አንጋፋ እና ስመጥር ትምህርት ቤት ስለሆነ ወደፊትም ስሙን እንደተጠበቀ እንዲቀጥል የሁላችንም አስተዋጽኦ ያስፈልጋል. ሲሉ አቶ ይልቃል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተናግረዋል
በዕለቱም የገዳሙ አስተዳዳሪ መጋቤ ኅሩያን አባ ኤልያስ በልሁ ገዳሙ ጥንታዊ እና ታሪካዊ ገዳም እንደመሆኑ መጠን በልማት ዘርፉም ባለው አቅም እየተንቀሳቀሰ በመሆኑ እና በአጠቃላይ ገዳሙ እና በተቋማቱ በተፈጠሩት የሥራ እድሎች ከ380 በላይ የሚሆኑ ሰራተኞችን አቅፎ የያዘ ታላቅ ገዳም እንደሆነ ትምህርት ቤቱ ታላላቅ ሰዎችን የሀገር ባለውለታዎችን ያፈራ እና በዚህ ትምህርት ቤት የተማሩ በተለያየ ትልልቅ ቦታዎች የሚገኙ ከዚሁ ትምህርት ቤት የተማሩ በርካታ ተማሪዎችን ለቁም ነገር ያበቃ አንጋፋ ትምህርት ቤት እንደሆነ ገልጸው ለተደረገው ድጋፍ በገዳሙ እና በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም የበላይ ኃላፊ ስም ምስጋና አቅርበዋል
በመቀጠልም አቶ ወርቁ አሸናፊ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልማት ተራድኦ ኮሚሽን ትምህርት ቤታችንን ሲያግዝ ይህ ለመጀመሪያ አይደለም ከዚህ በፊት በተለያዩ አጋጣሚዎች ድጋፍ አድርጋችሁልናል በዛሬው ዕለትም ያደረጋችሁልን እገዛ ከልብ የመነጨ ምስጋናችንን እናቀርባለን ሲሉ ገልጸዋል ።
በመጨረሻም ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ትምህርት ቤቱ የተከበረ ትምህርት ቤት ነው ብዙ ወላጆች ልጆቻቸውን ማስተማር የሚፈልጉበት ትምህርት ቤተ የመጀመሪያ ምርጫቸው ነው ይህ ተፈላጊነቱ ደግሞ ለትምህርት አስፍላጊውን ሥራ በመስራታችሁ ነው በተለያየ አጋጣሚ ስለ ትምህርት ቤቱ የምንሰማው መልካም ነገሮች ያስደስታሉ የቀደሙ አባቶቻችን ይህንን ሥርዓት ሰርተውልናል እኛም ዛሬ ላይ ይህን ነገር ማስቀጠል አለብን ።
ገዳሙ በአሁኑ ሰዓት የተለያዩ ልማቶችን እያለማ ይገኛል በርትታችሁ ከግብ ማድረስ መቻል አለባችሁ ሲሉ አባታዊ መመሪያ አስተላልፈዋል ።
© ምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም










