ሚያዚያ ፮ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም
“””””””””””””””””””””””””””
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
******
የ፳፻ ፲ወ ፭ ዓ.ም የገብረ ሰላመ በዐል በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ፣ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ፣ክቡር ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት መ/ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የጠቅላይ ቤተክህነት የየመምሪያውና የየድርጅቶቹ ኃላፊዎች፣ክቡር ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ ጸጋዬ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ አምባሳደር ሬሚ Remi Marechaux በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር፣የአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች፣ምዕመናንና ምዕመናት በተገኙበት በታላቅ መንፈሳዊ ሥነሥርዓት ተከብሯል።

በበዓሉ ላይየደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ቤተክርስቲያን ካህናትና ሊቃውንት መሪነት ጸሎተ ወንጌል ከደረሰ በኋላ”ወለመልአከ ሕይወትሰ” የሚለውን ሰላሞ በመምራት ዘምረዋል።የሰንበት ትምህርት ቤቶች አባላትም በዓሉን በተመለከተ መዝሙር አቅርበዋል።

በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ መልካም ፈቃድ ብፁዕ አቡነ ቶማስ የአዊ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ትምህርተ ወንጌል ሰጥተዋል።በመጨረሻም ቅዱስ ፓትርያርኩ ትምህርተ ወንጌል፣ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ከሰጡ በኋላ ለበዓሉ የተዘጋጀው ቄጤማ በቅዱስነታቸው ተባርኮ በበዓሉ ላይ ለተገኙ ሁሉ ታድሎ የበዓሉ ፍጻሜ ሆኗል።