ጥቅምት 27 ቀን 2017 ዓ.ም
++++++++++++++++++++++++
የደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት ርእሰ ከተማ በሆነችው ደሴ ከተማ በደሴ ርእሰ አድባራት ደብረ መድኃኒት መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን የደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መምህር አባ ለይኩን ወንድ ይፍራው፣ የደሴ ከተማ አስተዳደር ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ጠበብት ሲራክ መለሰ፣ የሀገረ ስብከቱና የአስተታደር ቤተ ክህነቱ የልዩ ልዩ ክፍል  ኃላፊዎች፣ የደሴ ከተማ አድባራት ሊቃውተ ቤተ ክርስቲያን፣ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች፣ በርካታ ቁጥር ያላቸው ምእመናንና ምእመናት በተገኙበት በታላቅ ድምቀት እየተከበረ ይገኛል፡፡

በበዓሉም ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን “መድኃኔ ዓለም እግዚአብሔር ኀደረ ላእሌሃ ኪያሃ ዘሠምረ ሀገረ” የሚለውን ያሬዳዊ ዜማ ያቀረቡ ሲሆን በመቀጠልም የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች “እስመ ውእቱ ክብሮሙ ለቅዱሳን አሰርገዋ ለምድር በጽጌያት የሚለውን ወረብ በተመሳሳይ አቅርበዋል፡፡

በደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ በመምህር አባ ለይኩን ወንድ ይፍራው “እግዚአብሔርሰ ንጉስ ውእቱ እምቅድመ ዓለም ወገብረ መድኃኒተ በማዕከለ ምድር የሚለውን ኃይለ ቃል መነሻ በማድረግ እግዚአብሔር አምላካችን ዘላለማዊ ንጉሥ ስለመሆኑ፣ መድኃኒት ስለመሆኑና ዓለምን ያፀና መሆኑን በቅደም ተከተል በመግለጽ ሰፊ ትምህርተ ወንጌል የተሰጠ ሲሆን ከዚሁ ጋር ተያይዞ በርካታ መንፈሳዊና ማኅበራዊ መልእክቶች ተላልፈው ጸሎተ ቡራኬ ተሰጥቶ በዓሉ በሰላም ተጠናቋል፡፡

ለሚቀጥለው ዓመት በሰላም ያድርሰን!!!

መረጃው የደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት ሕዝብ ግንኙነት ክፍል፡፡