የካቲት ፳፰ቀን፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም
“””””””””””””””””””””””””””
አዲስ አበባ-ኢትዮጵያ
***
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የመገናኛ ብዙሃን ሥርጭት ድርጅትና የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ በተናጠልና በጥምረት በዚህ በፈተና ወቅት በርካታ ውጤታማ ሥራዎችን በማከናወን የሚያስመሰግን ሥራ በመስራታቸውን ጉባኤ አድናቆቱን ገልጿል።

በቀጣይ ጊዜ በሁለቱ ተቋማት በጥምረትና በተናጠል መሰራት ያለባቸው ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎችን ጉባኤው ያመላከተ ሲሆን በተለይም መረጃዎችን የማሰባሰብ፣ወቅታዊ ምላሽ የመስጠትና በየዕለቱ የዜና ሽፋን የመስጠት ጉዳይ ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሰራ አቅጣጫ አስቀምጧል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘም የቤተክርስቲያናችን የውጭ ግንኙነት መምሪያም ዓለም አቀፉ ማኅበረ ሰብ የተፈጠረውን ሃይማኖታዊ፥ ቀኖናዊና አስተዳደራዊ ጥሰት እንዲረዳና እንዲያወግዘው ለማድረግ ላደረገው ጥረትና ላስመዘገበው ውጤት በጉባኤው ምስጋና ተችሮታል።

በመጨረሻም ለኢ/ኦ/ተ/ቤ/መገናኛ ብዙሃን ሥርጭት ድርጅት እና ለሕዝብ ግንኙነት መምሪያው ሥራ መሳለጥ የሚያስፈልጋቸው የሰው ኃይል እንዲሟላላቸው ጉባኤው ወስኗል።