የጥምቀት በዓልን በኖርዌይ ዋና ከተማ ኦስሎ ማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተክርስቲያን
የ2015 ዓ/ም የከተራ እና የጥምቀት በዓልን በኖርዌይ ዋና ከተማ ኦስሎ ማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተክርስቲያን ለማክበር ዓርብ ምሽት የተጓዙት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ እና የኒውዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ቆይታቸውን በመግታት ወደ አዲስ አበባ ገቡ። ብፁዕነታቸው ቅዳሜ እና እሑድ በኦስሎ ማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተክርስቲያን አዘጋጅነት የበርገን፣ ክርሰቲያንሳንድ፣ ስታቫንገር እና ትሮንድሀይም አብያተ ክርስቲያናት በጋራ የሚያከብሩትን የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን በዓለ ጥምቀት ለማክበርና አባታዊ ቡራኬ ለመስጠት ተጉዘው በዓሉ በደመቀ መንፈሳዊ አገልግሎት የተከበረ ሲሆን ወቅታዊውን የቤተክርስቲያን ችግር አስመልክቶ የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ስብሰባ በቅዱስ ፖትርያርኩ በመጠራቱ መቆይታቸውን በማቋረጥ ዛሬ ጠዋት አዲስ አበባ ገብተዋል።