ኅዳር ፳፩ ቀን ፳፻፲ወ፮ ዓ.ም
*******
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
=============

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ጥቅምት ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አስተዳደራዊ ችግሮችን በመቅረፍ ለሀገረ ስብከቱ የቤተክርስቲያናችንን ሕጎችና መመሪያዎችን መሰረት ያደረገ ራሱን የቻለ መተዳደሪያ ደንብ በባለሙያዎች እንዲዘጋጅለት በማድረግና ደንቡን መርምሮ በማጽደቅ ወደ በሥራ ላይ እንዲውል ውሳኔ መስጠቱ ይታወሳል።

በዚህ ቅዱስ ሲኖዶስ ባጸደቀው ደንብ መሰረት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት በሀገረ ስብከቱ ላይ ያለውን ሥልጣንና ኃላፊነት ባለመረዳትና ደንቡን በቅጡ ባለማንበብ አንዳንዶች በሚዲያ ጭምር ጠቅላይ ቤተክህነቱ በሀገረ ስብከቱ አስተዳደራዊ ጉዳይ እንደማይመለከተው ሲገልጹ ይስተዋላሉ ለመሆኑ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት መተዳደሪያ ደንብ ስለ ጠቅላይ ቤተክህነት ሥልጣንና ኃላፊነት ምን ይላል የሚለውን ከተለያዩ የደንቦቹ አንቀጾች ስክሪን ሹት በማድረግ የለጠፍነውን እንድትመለከቱት እየጋበዝን ቀሪውን ክፍል ደንቡን በማንበብ መገንዘብ እንደምትችሉ
ከወዲሁ በክብር እናሳስባለን።