የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ፲ኛ ዓመት በዓለ ሢመት በታላቅ ድምቀት ተከብሮ ዋለ።

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ፲ኛ ዓመት በዓሉ ሢመት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በታላቅ ሥነሥርዓት ተከብሮ ውሏል።በበዓሉ ላይ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጠቅላይ ጸሐፊ ሊቀ ቴጉሃን ታጋይ ታደለ የጠቅላይ ቤተክህነት የመምሪያና የድርጅትኃላፊዎች፣የአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች ተገኝተዋል።

የቅዱስነታቸውን ፲ኛ ዓመት በዓለ ሢመት በማስመልከት የተዘጋጀው “ዜና መዋዕል ዘብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክና ቃለ በረከት ዘብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ መጻህፍት በዛሬው ዕለት ተመረቀ።

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖትን ፲ኛ ዓመት በዓለ ሢመት በማስመልከት በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት በተቋቋመው የሥነ ጽሑፍ ዝግጅት ኮሚቴ ተዘጋጅቶና በሊቃውንት ጉባኤ ተመርምሮ የተዘጋጀውና ለህትመት የበቃው ዜና መዋዕል ዘብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ መጽሐፍና የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ቃለ በረከት መጽሐፍ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ሚኒስትሮች ፣አምባሳደሮች፣የጠቅላይ ቤተክህነት የመምሪያና የድርጅት ኃላፊዎች፣የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ኃላፊዎች፣የአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች ፣የወጣት ማኅበራት ተወካዮችና የክብር እንግዶች በተገኙበት ዛሬ የካቲት ፳፫ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም በታላቅ ድምቀት ተመርቋል።

ቅዱስነታቸው በብፁዕ አቡነ ዮሐንስ የሽኝት መርሐ ግብር ላይ ለመገኘት ዛሬ ማለዳ መቐለ ገብተዋል።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት መቐለ አሉላ ኣባነጋ አለም አቀፍ አየር ማረፍያ በሰላም ገብተዋል ።

የብፁዕ አቡነ ዮሐንስ የሕይወት ታሪክ

ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ ትሕትናን፣ አፍቅሮ ቢጽን፣ አክብሮ ሰብእን ዓላማ አድርገው የሚኖሩ በካህናት፣ በምእመናንና በተማሪዎቻቸው ዘንድ ተወዳጅነት ያላቸው፣ በአባትነታቸው ብዙ ፍቅርን ያተረፉ በአጠቃላይ በአርአያነታቸውና በገብረ ገብነታቸው በሁሉም ዘንድ ክብር ያገኙ ደግ አባት ናቸው፡፡