የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

የብፁዕ አቡነ ዮሐንስ የሕይወት ታሪክ

March 1, 2023

ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ በክልል ትግራይ በማዕከላዊ ዞን በዓድዋ ወረዳ ልዩ ስሙ የሐ ደብረ ሐመልማል (መዝብር) በተባለው ቀበሌ ሚያዝያ 20 ቀን 1928 ዓ.ም ከአባታቸው ከአለቃ
ኃይሉ ወልደ ማርያምና ከእናታቸው እመት ዘነበች ወልደ ማርያም ተወለዱ፡፡

ዕድሜያቸው ለትምህርት እንደደረሰ ከአጎታቸው ከቄስ ገብረ ሕይወት ወ/ማር ያም ትምህርት ጀምረው ትምህርቱ እየገባቸው ሲሄድ ወላጆቻቸው መሪ ጌታ ተክለ ጊዮርጊስ ከሚባሉ መምህር አስገብተዋቸው ንባብና የቃል ትምህርት በማጠናቀቅ የግብረ ዲቁናን ትምህርት ተማሩ፡፡

ሆኖም የትምህርት ፍላጐታቸው እየ ተጠናከረ በመሄዱ የፈለጉትን ትምህርት ለመከታተል ከትውልድ አገራቸው ወጥተው ደብረ ዓባይ ወደሚባለው የመዝገበ ቅዳሴ ማስመስከሪያ የአብነት ቦታ ገዳም በመሄድ ምስክር ከሆኑት ሊቅ ከመምህር የኋላሸት መንገሻ ምዕራፍ ጾመ ድጓ፣ ባሕረ ሐሳብና የመዝገበ ቅዳሴን የዜማ ትምህርት ልኩን፣ አመሉንና ተቃራኒውን ለይተው ለመምህርነት በሚያበቃ ደረጃ ስለወሰነት በመምህርነት ተመርቀዋል፡፡

ከዚያም በኋላ በዚሁ ገዳም ቅዳሴ እያስተማሩ ከመሪጌታ መጽሔት ቅኔ ተምረዋል፡፡ በዚህም ሳይወሰኑ የቅኔ ሞያቸውን ለማዳበር ከደብረ ዓባይ ተነሥተው ወደ ጎንደር ክፍለ ሀገር በመሄድ በሊቅነታቸው ከታወቁት ከመምህር አክሊሉ ገ/ሥላሴ ዘንድ ቅኔ ቤት ገብተው ለአምስት ዓመት ያህል ቅኔ ከነአገባቡ ከመማራቸውም በላይ የዳዊትንና የፍትሐ ነገሥትን ትርጓሜንም ከርሳቸው አሂደዋል፡፡

ከዚያም ወደነበሩበት ገዳም ወደ ደብረ ዓባይ ተመልሰው በዚያው ቅዳሴ እያስተማሩ ለ7 ዓመታት ያህል ከየኔታ የኋላሸት ጉባኤ መጻሕፍት ሐዲሳትን አሄደዋል፡፡ በዚህም ትምህርታቸውን እንዳጠናቀቁ ወደ ትውልድ አገራቸው ተመልሰው አቡነ መዝራዕተ ክርስቶስ ገዳም ወንበር ዘርግተው ጉባኤ አስፍተው ለ12 ዓመታት ያህል በአፍለኛው ጉባኤያቸው ጠንክረው በማስተማር ብዙ ዲያቆናትን፣ ቀሳውስትንና መምህራንን አፍርተዋል፡፡

ቀጥሎም መምህራቸው የኔታ የኋላሸት በ1962 ዓ.ም ታኅሣሥ 13 ቀን ስለ ዐረፉ በእሳቸው እግር ተተክተው ሲያስተምሩ ከቆዩ በኋላ የትግራይ ክፍለ ሀገር ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ በመቀሌ ከተማ ያሠሩት ከፍተኛ መንፈሳዊ ኮሌጅ የካህናት ማሠልጠኛ አዳሪ ቤት ስለሆነ ለቤተ ክርስቲያናችን ብዙ ፍሬ የሚያፈሩ መሆናቸውን በመግለጽ ደጋግመው ስለጻፉላቸው፣ አስጠርተውም ስለነገሩዋቸው ቀደም ሲል ከቦታው አብረዋቸው ከየኔታ የኋላሸት የተማሩ አባት ቄሰ ገበዝ ገብረ ሊባኖስን ተክተው በ1963 ዓ.ም ወደ መቀሌ መጡ፡፡

ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ጉባኤ አስፍተው በከሳቴ ብርሃን ሰላማ መንፈሳዊ ኮሌጅና በደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል በማስተማር ላይ እንዳሉ ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በ1975 ዓ.ም አገልግሎታቸውንና ትጋታቸውን ተመልክተው መልአከ ሰላም በማለት የመዐርግ ስም ሰጥተው በመምህርነታቸው ላይ በተደራቢነት የደብረ ሰላም ቅ/ሚካኤል ካቴድራል አስተዳዳሪ አድርገው ሾመዋቸዋል፡፡

በዚህ ካቴድራልም ለ22 ዓመታት በሰላም የኖሩ ሲሆን የማስተማሩ ሥራ እንደተጠበቀ በሳቸው አመራር በርካታ የልማት ሥራዎች ተሠርተዋል፡፡

ጥቂቶቹንም ለመግለጽ የደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ዮሐንስ የተሠራ ቢሆንም ብዙ ነገር ይጎድለው ስለነበር
• አጥሩ በሚገባ እንዲታጠር፣
• በብፁዕ አቡነ ዮሐንስ የተጀመረው ትልቁ ደወል ቤት ከፍጻሜ እንዲደርስ፣
• ትልቅ የሰንበት ት/ቤት አዳራሽ፣
• የብፁዕ አቡነ ዮሐንስ ሙዝየም (ቤተ መዘክር)፣
• የቅዱስ ፓትርያርክና የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ማረፊያ ቤት፣
• የቤተ ክርስቲያኑ ቆርቆሮ እንዲቀየር፣ ምንጣፍ እንዲነጠፍ አድርገዋል፤ ሌሎችንም አስፈላጊ እድሳቶች አሳድሰዋል፤ እንዲሁም የቤተ ክርስቲያኑ አገልጋይ ካህናትን መኖርያ ቤት አሠርተዋል፡፡

ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ ልክ እንደስማቸው ከሊቅ እስከ ደቂቅ የሰላም አባት በመሆን ለ22 ዓመት ሲያስተዳድሩ በካቴድራሉ አገልጋይ ካህናት ዘንድ እንዳያጥዋቸው ከመጨነቅ በቀር ምንም ዓይነት እክል ገጥሟቸው አያውቅም፤ የሰላም አባት የመሆናቸውን ያህል ሁሉም አባታዊ ፍቅር በተላበሰ መልኩ ያከብራቸዋል፤ ትእዛዛቸውን ያከብራል፤ ምክራቸውን ይቀበላል፣ በብፁዕ አቡነ ዮሐንስ ዘንድ እንደ አስተዳዳሪ ማዘዝ ብቻ አይታሰብም፣ ‹‹ዘይከውን ሊቀ ይኩንክሙ ላእከ›› የሚለውን አምላካዊ ቃል በመከተል

• በልማት ሥራ፣
• በማኅሌት፣ በሰዓታት፣
• በቅዳሴ፣
• በስብከተ ወንጌልና በማንኛውም የቤተ ክርስቲያኒቱ አገልግሎት ከተራው አገልጋይ ቀድሞ መገኘት የዘወትር ተግባራቸው ነው፡፡

ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ ከላይ እንደተጠቀሰው ሞያቸው የቅዳሴ ትምህርት ብቻ አይደለም፤ የመጻሕፍተ ሐዲሳት ሞያም ስላላቸው ለ33 ዓመታት ከሊቀ ሊቃውንት ያሬድ ካሣ ጋር በመሆን የመዝሙረ ዳዊትን፣ የመጻሕፍተ ሐዲሳትን፣ የፍትሐ ነገሥትን እንዲሁም የውዳሴ ማርያምን፣ የቅዳሴ ማርያምን ጉባኤ በመምራት አንድ ቀን ሳይለዩ ትሕትናቸውን፣ ትዕግሥታቸው ንና መልካም ምሳሌነታቸውን ያሳዩ ተወዳጅ አባት መምህር ናቸው፡፡ ብፁዕ አቡነ ዮሐንስም እጅግ አብልጠውና አልቀው ይወዱዋቸው ስለነበር ሁሉ ጊዜ ይጐበኛቸው ነበር፡፡

ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ በታወቀው የመዝገበ ቅዳሴ ሞያቸው በተሰጣቸው የመዓዛ ክህነት ሀብት ልዩ ተሰጥዎ ያላቸው ድምፃዊ ከመሆናቸው የተነሣ ከጥንት ከአበው ሲያያዝ የመጣውን የደብረ ዓባይ ባሕል የቅዳሴ ዜማ አብነት ግእዙና ዕዝሉ እንዲሁም አራራዩና አንቀጹ ሳይቀር በሙሉ በዘመናዊ መሣሪያ የድምፅ መቅረጫ ቴፕ ተቀርጾ በቅርስነት ለትውልድ ይተላለፍ ዘንድ የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ባዘዙት መሠረት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ ድምፃቸው ተቀርጾ ተሰራጭቷል ፤ በዚህም ከፍተኛ አገልግሎት ለቤተ ክርስቲያን ማበርከታቸውን በመረዳት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የመታሰቢያ ስጦታ የአንገት አይከል ዕፀ መስቀል ሸልመዋቸዋል፡

ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ በ1940 ዓ.ም ማዕርገ ዲቁናን ከብፁዕ አቡነ ማርቆስ ጳጳስ ዘኤርትራ፤ በ1946 ዓ.ም መዐርገ ምንኵስናን ከመምህር ዘሚካኤል ዘደብረ ዓባይ ገዳም መምህር፣ (አበምኔት) በ1949 ዓ.ም መዐርገ ቅስናን ከብፁዕ አቡነ ሚካኤል ዘጎንደር በ1969 ዓ.ም መዐርገ ቁምስናን ከብፁዕ አቡነ ዮሐንስ ዘትግራይ ተቀብለው በእነዚህ ሁሉ የክህነት መዐርጋት መንፈሳዊውን አገልግሎት እየሰጡ በንጽሕና በድንግልና የኖሩ አባት ናቸው፡፡

ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ ትሕትናን፣ አፍቅሮ ቢጽን፣ አክብሮ ሰብእን ዓላማ አድርገው የሚኖሩ በካህናት፣ በምእመናንና በተማሪዎቻቸው ዘንድ ተወዳጅነት ያላቸው፣ በአባትነታቸው ብዙ ፍቅርን ያተረፉ በአጠቃላይ በአርአያነታቸውና በገብረ ገብነታቸው በሁሉም ዘንድ ክብር ያገኙ ደግ አባት ናቸው፡፡

ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ ይህን በመሰለው ቅድስናቸው፣ በቤተ ክርስቲያን ትምህርት እውቀታቸው፣ በተለይም በመዝገበ ቅዳሴ የአብነት መምህርነታቸው አያሌ የቤተ ክርስቲያን አባቶችን በማፍራታቸውና ባበረከቱት የረዥም ዘመን ቅድስናን የተመላ አገልግሎት ፍጹም አባትነታቸው ተመዝኖ ብቁ ሆነው በመገኘታቸው ሐምሌ 9 ቀን 1997 ዓ.ም በተደረገው የጳጳሳት ምርጫ ከሌሎች ዕጩ ቆሞሳት ጋር ተወዳድረው ባገኙት የድምፅ ብልጫ የመቀሌ ደብረ ሰላም ቅ/ሚካኤል ካቴድራልና የከሣቴ ብርሃን ሰላማ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ኃላፊ ጳጳስ ሆነው እንዲሠሩ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ተመርጠው ሐምሌ 22 ቀን 1997 ዓ.ም በብፁዕ ቅዱስ አቡነ ጳውሎስ (ዶ/ር) ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዕጅ ተሹመዋል።

ብፁዕነታቸው በተመደቡበት ኃላፊነት በቅንነት ሲያገለግሉ ቆይተው ዛሬ የካቲት 21 ቀን 2015 ዓ.ም ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።

የብፁዕነታቸው በረከት ይደርብን!

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አዲስ የተሠራውን የለገዳዲ አንቀጸ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን መረቁ፡፡
  • የወጨ አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አዲሱ ሕንጻ በብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቦሌ ምዕራፈ ሰማዕታት ወደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የተከናወነው የወንዝ ማስቀየስ ሥራ ተጠናቆ በብፁዓን አባቶች ቡራኬ ተመረቀ።
  • በሸገር ሀገረ ስብከት የታነጸው የደብረ ሣህል ቅዱስ ገብርኤል አዲሱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ጸሎተ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሱማሌ ክልል ጅግጅጋ እና የምስራቅ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በምሥራቅ አርሲ አሰላ ከተማ ደብረ ምጽላል ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: “አባ ” ንዋየ ሥላሴ የተባሉት በፈቃዳቸው ይቅርታ ጠየቁ እንጂ “ያፈነም” “ያስገደደም” አካል የለም ይህ የሐሰት ወሬ ነው ከዚህ ይልቅ በሕገወጥ መንገድ ያላችሁ አካላት በይቅርታ ወደ ቤታችሁ መመለሱ ይበጃል” Link to: “አባ ” ንዋየ ሥላሴ የተባሉት በፈቃዳቸው ይቅርታ ጠየቁ እንጂ “ያፈነም” “ያስገደደም” አካል የለም ይህ የሐሰት ወሬ ነው ከዚህ ይልቅ በሕገወጥ መንገድ ያላችሁ አካላት በይቅርታ ወደ ቤታችሁ መመለሱ ይበጃል” “አባ ” ንዋየ ሥላሴ የተባሉት በፈቃዳቸው... Link to: ቅዱስነታቸው በብፁዕ አቡነ ዮሐንስ የሽኝት መርሐ ግብር ላይ ለመገኘት ዛሬ ማለዳ መቐለ ገብተዋል። Link to: ቅዱስነታቸው በብፁዕ አቡነ ዮሐንስ የሽኝት መርሐ ግብር ላይ ለመገኘት ዛሬ ማለዳ መቐለ ገብተዋል። ቅዱስነታቸው በብፁዕ አቡነ ዮሐንስ የሽኝት መርሐ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top