የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

የመቱ ፈለገ ጥበብ መንፈሳዊ ኮሌጅ የመጀመሪያውን ዙር እጩ መምህራን በደማቅ ሥነ ሥርዓት አስመረቀ

July 21, 2026
ሐምሌ ፲፬ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም.| ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
​ከተቋቋመ ገና ሦስት ዓመታትን ያስቆጠረው የመቱ ፈለገ ጥበብ መንፈሳዊ ኮሌጅ፤ ከተለያዩ አህጉረ ስብከቶች ተቀብሎ ሲያሰለጥናቸው እና ሲያስተምራቸው የቆያቸውን ፲፰ እጩ መምህራን ደቀ መዛሙርት በሐምሌ ፲፩ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም. በደመቀ ሥነ ሥርዓት አስመርቋል።
ይህ ታሪካዊ የምረቃ በዓል የመቱ ፈለገ ጥበብ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ኃላፊ፣ ፕሬዚዳንትና የኢሉ አባ ቦር እና የምዕራብ ወለጋ አህጉረ ስብከቶች ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ (ዶ/ር)፣ የቡኖ በደሌ እና የቄለም ወለጋ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም፣ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ትጉሃን ብርሃኑ መንገሻ፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የተመራቂ ቤተሰቦች በተገኙበት ተካሂዷል።
​በመርሐ ግብሩ ላይ በረከታቸው ይደርብንና ታላቁና ጸሎተኛው የቀድሞው የሀገረስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሚካኤል ኮሌጁ በአፋጣኝ እንዲከፈት መመሪያ በመስጠትና ጥብቅ ክትትል በማድረግ፣ በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ መሠረት መንሳዊ ኮሌጁ እንዲመሠረት ያደረጉት ጥረትና የነበራቸው አባታዊና መምህራዊ ምክር በታላቅ አክብሮት ተዘክሯል።
የኮሌጁ የበላይ ኃላፊና ፕሬዚዳንት ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ (ዶ/ር) ለአዲሶቹ እጩ መምህራን ባስተላለፉት አባታዊ አደራና ቃለ ቡራኬ፤ “ዛሬ የተሰበሰብነው ትምህርት ያበቃበትን ቀን ለማክበር ወይም የዲፕሎማና የዲግሪ ወረቀት ለመስጠት ሳይሆን፣ የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ቀዳሚ ዓላማና የወንጌል አገልግሎት አደራ ለመቀበል ነው” ሲሉ ገልጸዋል።
ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትና የቤተ ክርስቲያኒቱ መሪዎችም ተመራቂዎቹ በሄዱበት ሁሉ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በታማኝነትና በቅንነት እንዲያገለግሉ፣ የተማሩትን በሥራ እንዲገልጡና የተዘጉትን አብያተ ክርስቲያናት እንዲያስከፍቱ ጥብቅ አደራ አስተላልፈዋል።
​ተመራቂ ደቀ መዛሙርቱም በበኩላቸው ባስተላለፉት የጋራ መልእክት፤ በኮሌጁ የቆይታ ጊዜያቸው በመንፈሳዊ ዕውቀትና በሥነ ምግባር ታንጸው፣ በሚያምኑትና በማያምኑት ዘንድ የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት በመሆን በሕይወታቸው ተነባቢ መጽሐፍ ሆነው መኖርንና ሐዋርያዊ ግዴታቸውን መወጣትን እንደተረዱ ገልጸዋል። አያይዘውም “ከዚህ በኋላ የፍጥረት ሁሉ መዳኛ የሆነውን ወንጌል ይዘን የምናስተምርበት፣ ጨለማውን ዓለም የምናበራበት፣ የታመመውን የምናክምበት እንዲሁም በቃልም ሆነ በሥራ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ተልዕኮ የምንፈጽምበት ጊዜ ነው፤ ትምህርት አላለቀም፣ በማስተማር ውስጥ መማር በመማር ውስጥ ማስተማር ይቀጥላል፤ በቀጣይ ሕይወታችን በሁለት ወገን የተሳለ ሰይፍ፣ እንደ እባብ ልባም እንደ እርግብም የዋህ ሆነን አገልግሎታችንን እንፈጽማለን” ሲሉ ቃላቸውን አድሰዋል።
​በዕለቱ መርሐ ግብር ላይ በኮሌጁ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የተዘጋጀችው “መጽሔተ ጥበብ ቁጥር ፩” የተሰኘችው መጽሔት ተመርቃ ለአገልግሎት የበቃች ሲሆን፤ በኮሌጁ የሚገኙ የአስተዳደር፣ የመምህራንና የድጋፍ ሰጪ አካላት ደቀ መዛሙርቱ በውጤታማነት እንዲመረቁ ላደረጉት ታላቅ አስተዋጽኦ ዕውቅና ተሰጥቷል። በሥነ ሥርዓቱ ማጠቃለያ ላይም ለኮሌጁ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት፣ ለደቀ መዛሙርቱና በከፍተኛ ውጤት ለተመረቁ ተመራቂዎች የምስክር ወረቀትና የክብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
​ዘገባው፦ የኢሉ አባ ቦር ሀገረ ስብከት ሚዲያ
‎
Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/pr000049.jpeg 278 448 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-07-21 10:54:282026-07-23 10:56:39የመቱ ፈለገ ጥበብ መንፈሳዊ ኮሌጅ የመጀመሪያውን ዙር እጩ መምህራን በደማቅ ሥነ ሥርዓት አስመረቀ
Search Search

Recent Posts

  • የድሬዳዋ ሳባ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ያስገኘባው ባለ ሦስት ወለል ሁለገብ ሕንጻ በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና በብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ጸሎተ ቡራኬ በዛሬው ዕለት ተመረቋል።
  • የቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ሕንጻ ቤተክርስቲያን ዕድሳት ተጠናቆ በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው ተባረከ።
  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ የሚመራ የቤተክርስቲያናችን ልዑክ ወደ ቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ተጓዘ።
  • አሐዱ ባንክ ላደረገው ሁለተናዊ እገዛ በቋሚ ሲኖዶስ የእውቅናና የምስጋና ምስክር ወረቀት ተበረከተለት።
  • የመቱ ፈለገ ጥበብ መንፈሳዊ ኮሌጅ የመጀመሪያውን ዙር እጩ መምህራን በደማቅ ሥነ ሥርዓት አስመረቀ

Archives

  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: የጋርመንት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አዲስ የሕንጻ ግንባታ የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ፤ ከ5.7 ሚሊዮን ብር በላይ የወጣባቸው የልማት ሥራዎች ተመረቁ። Link to: የጋርመንት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አዲስ የሕንጻ ግንባታ የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ፤ ከ5.7 ሚሊዮን ብር በላይ የወጣባቸው የልማት ሥራዎች ተመረቁ። የጋርመንት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን... Link to: አሐዱ ባንክ ላደረገው ሁለተናዊ እገዛ በቋሚ ሲኖዶስ የእውቅናና የምስጋና ምስክር ወረቀት ተበረከተለት። Link to: አሐዱ ባንክ ላደረገው ሁለተናዊ እገዛ በቋሚ ሲኖዶስ የእውቅናና የምስጋና ምስክር ወረቀት ተበረከተለት። አሐዱ ባንክ ላደረገው ሁለተናዊ እገዛ በቋሚ ሲኖዶስ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top