የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

የጋርመንት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አዲስ የሕንጻ ግንባታ የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ፤ ከ5.7 ሚሊዮን ብር በላይ የወጣባቸው የልማት ሥራዎች ተመረቁ።

July 19, 2026
ሐምሌ 12 ቀን 2018 ዓ.ም.
የጋርመንት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ለአዲስ ለሚገነባው የሕንጻ ግንባታ የመሠረት ድንጋይ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም የበላይ ኃላፊ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ፣ የምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ተገኝተው የመሠረት ድንጋዩን የባረኩ ሲሆን፣ የተጠናቀቁ የልማት ሥራዎችንም መርቀዋል።
የደብሩ ሰበካ ጉባኤ ጽሕፈት ቤት ባቀረበው ልማታዊ ሪፖርት መሠረት፣ ቤተ ክርስቲያኑ በ1997 ዓ.ም. በአነስተኛ መቃኞ ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ በየደረጃው እያደገ የመጣ ሲሆን፣ በ2017 በጀት ዓመት መጨረሻ ላይ 1.34 ሚሊዮን ብር ክፍያ በመፈጸም 1,350 ካሬ ሜትር ተጨማሪ ቦታ ወደ ደብሩ ይዞታ እንዲካተት አድርጓል።
በዕለቱ በብፁዕነታቸው የተመረቀውና ቀደም ሲል በአፈርና በገረጋንቲ ተራራ ተሸፍኖ ለጎርፍ አደጋ ተጋልጦ የነበረው የቤተ ክርስቲያኑ ዐውደ ምሕረት፣ በባለሙያ በተጠናው መሠረት ምዕራባዊ አቅጣጫውን የጠበቀና ደረጃውን የጠበቀ የመጠለያ፣ የቴራዞ፣ የኮብልስቶን ንጣፍና የውኃ ፍሳሽ ማስወገጃ ሥራዎች ተከናውነውለታል። ለነዚህ የዐውደ ምሕረት ማሻሻያና መጠለያ ሥራዎች በሰበካ ጉባኤውና አዲስ በተዋቀረው የልማት ኮሚቴ አማካኝነት፣ ከምዕመናን በዓይነት ከተገኘው ድጋፍ ጋር ተደምሮ በአጠቃላይ 5,788,538.92 (አምስት ሚሊዮን ሰባት መቶ ሰማንያ ስምንት ሺሕ አምስት መቶ ሠላሳ ስምንት ብር ከዘጠና ሁለት ሳንቲም) ወጪ መደረጉ ታውቋል።
ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ አቡነ ሳዊሮስ ባስተላለፉት አባታዊ መልእክት፤ የመጀመሪያውና ዋናው ልማት ወንጌል እንደሆነ ዐፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል። አክለውም “ለሕዝበ ክርስቲያኑ ቁጥር መጨመር ምላሽ የሚሰጥና ለትውልድ የሚተላለፍ አዲስ ሕንጻ ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ ባርከን አስቀምጠናል፤ ነገር ግን አዲስ ሕንጻ ሲታነጽ በዲዛይንና በጥራት ረገድ ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል” ብለዋል። ብዙ ገንዘብ ወጥቶበት ከተሠራ በኋላ የዲዛይን ችግርና የቦታ መጥበብ እንዳያጋጥም ሥራውን በቶሎ በመጀመር በጥራት እንዲያጠናቅቁ መመሪያ የሰጡት ብፁዕነታቸው፣ ቤተ መቅደስ ማነጽ የሚቻለው እግዚአብሔር ለፈቀደላቸው ብቻ በመሆኑ ምዕመናኑ የተሰጣቸውን ዕድል ተጠቅመው ጊዜ ሳያባክኑ እንዲረባረቡ አሳስበዋል።
የዕለቱን ትምህርተ ወንጌል የምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል “እግዚአብሔር በእውነት በዚህ ስፍራ አለ” (ዘፍ 28፥16) የሚለውን ኃይለ ቃል መነሻ በማድረግ ሰፊ ትምህርት ሰጥተዋል።
የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ መልአከ ሰላም ዓለማየሁ ተፈራ በበኩላቸው፤ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመሠረት ድንጋይ ያስቀመጧቸውን በርካታ አብያተ ክርስቲያናት መመሪያ በመስጠት ብቻ ሳይሆን በቅርበት ክትትል ስለሚያደርጉ፣ በጥራትና በአጭር ጊዜ ውስጥ ለአገልግሎት እንዲበቁ እያደረጉ መሆኑን ገልጸው፣ በዚህም ግንባታቸው ዘግይቶ የነበሩ በርካታ አብያተ ክርስቲያናት ተጠናቀው መመረቃቸውን አስታውሰዋል።
በዕለቱ በደብሩ ለተሠሩ የልማት ሥራዎች ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ምዕመናን የሽልማትና የምስጋና ሰርተፍኬት የተበረከተላቸው ሲሆን፣ በመርሐ ግብሩ ላይ የሀገረ ስብከቱ ዋና ጸሐፊ ሊቀ ስዩማን ተስፋዬ ለሜቻ፣ የሀገረ ስብከቱ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ ክፍል ኃላፊ መጋቤ ወንጌል ሄኖክ ታዬ፣ የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ጽዮን አባ ጳውሎስ ከበደ፣ የደብሩ ዋና ጸሐፊ ሊቀ ስዩም አክሊሉ፣ የደብሩ የሥራ ኃላፊዎች፣ ማኅበረ ካህናትና በርካታ ምዕመናን ተገኝተዋል።
በመጨረሻም መርሐ ግብሩ በጸሎት ተጠናቅቋል።
Miidiyaa Biyya Lallabaa Shaggar/የሸገር ሀገረ ስብከት ሚዲያ/
Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/pr000047.jpeg 269 448 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-07-19 15:12:002026-07-19 15:12:00የጋርመንት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አዲስ የሕንጻ ግንባታ የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ፤ ከ5.7 ሚሊዮን ብር በላይ የወጣባቸው የልማት ሥራዎች ተመረቁ።
Search Search

Recent Posts

  • የድሬዳዋ ሳባ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ያስገኘባው ባለ ሦስት ወለል ሁለገብ ሕንጻ በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና በብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ጸሎተ ቡራኬ በዛሬው ዕለት ተመረቋል።
  • የቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ሕንጻ ቤተክርስቲያን ዕድሳት ተጠናቆ በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው ተባረከ።
  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ የሚመራ የቤተክርስቲያናችን ልዑክ ወደ ቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ተጓዘ።
  • አሐዱ ባንክ ላደረገው ሁለተናዊ እገዛ በቋሚ ሲኖዶስ የእውቅናና የምስጋና ምስክር ወረቀት ተበረከተለት።
  • የመቱ ፈለገ ጥበብ መንፈሳዊ ኮሌጅ የመጀመሪያውን ዙር እጩ መምህራን በደማቅ ሥነ ሥርዓት አስመረቀ

Archives

  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: የሲኤምሲ ደብረ ጽባሕ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ካቴድራል ተብሎ ተሰየመ። Link to: የሲኤምሲ ደብረ ጽባሕ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ካቴድራል ተብሎ ተሰየመ። የሲኤምሲ ደብረ ጽባሕ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን... Link to: የመቱ ፈለገ ጥበብ መንፈሳዊ ኮሌጅ የመጀመሪያውን ዙር እጩ መምህራን በደማቅ ሥነ ሥርዓት አስመረቀ Link to: የመቱ ፈለገ ጥበብ መንፈሳዊ ኮሌጅ የመጀመሪያውን ዙር እጩ መምህራን በደማቅ ሥነ ሥርዓት አስመረቀ የመቱ ፈለገ ጥበብ መንፈሳዊ ኮሌጅ የመጀመሪያውን...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top