በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ የሚመራ የቤተክርስቲያናችን ልዑክ ወደ ቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ተጓዘ።
ሐምሌ ፲፮ ቀን ፳፻ ፲ወ፰ ዓ.ም አዲስአበባ -ኢትዮጵያበብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣
የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሚመራ የቤተክርስቲያን ልዑክ ወደ ቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ተጉዟል።
ከልዑካን ቡድኑ መካከል በፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ
ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ብፁዕ
አቡነ መልከጼዴቅ የጉራጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ብፁዕ
አቡነ ገብርኤል የምዕራብ ሸዋ ሀገረ ርብከት ሊቀ ጳጳስ ፣
የጠቅላይ ቤተክህነት የየምምሪያው ኃላፊዎች ይገኙበታል።
የልዑክ ቡድኑ ወደ ቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም የተጓዘው ዓመታዊውን የቅዱስ ገብርኤል በዓልን ለማክበርና ከሰባ ዓመታት አገልግሎት በኋላ ከፍተኛ ጉዳት ላይ ደርሶ የነበረው የቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ሕንጻ ቤተክርስቲያን ታድሶ በመጠናቀቁ ታቦተ ሕጉን ወደ መንበረ ክብሩ ለመመለስና በምርቃት መርሐ ግብሩ ላይ ለመገኘት ነው።
በዚህም መሰረት ብፁዓን አባቶቹ በዛሬው ዕለት በገዳሙ ተገኝተው ታቦተ ሕጉን ወደ መንበረ ክብሩ የሚያስገቡ ሲሆን የታደሰው ሕንጻ ቤተክርስቲያንም ይመረቃል።
በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ ሥራ አስኪያጁ የሚመራው የቤተክርስቲ ያናችን ልዑክ ድሬዳዋ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ ክቡር አቶ ሀርቢ ቡህ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ፣ብፁዕ አቡነ በርተሎሜዎስ የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ኒቆዲሞስ የምሥራቅ ሐረርጌ ሀገ፣ረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ብፁዕ አቡነ እንጦንስ የምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ካህናትና ሰንበት ተማሪዎች በዝማሬ አቀባበል ያደረጉለት ሲሆን የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደርም በክብር ዘብና በማርሽ ባንድ የታጀበ ደማቅ አቀባበል አድርጎለታል።