የቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ሕንጻ ቤተክርስቲያን ዕድሳት ተጠናቆ በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው ተባረከ።
ሐምሌ ፲፮ ቀን ፻፻ ፲ወ፰ ዓ.ም ቁልቢብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣
የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከሰባ ዓመታት አገልግሎት በኋላ የታደሰውን የቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ሕንጻ ቤተክርስቲያን ባርከው ታቦተ ሕጉን ወደ መንበረ ክብሩ አስገቡ።
በመርሐ ግብሩ ላይ ብፁዕ አቡነ እንጦንስ የምዕራብ ሐረርጌ
ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ብፁዕ አቡነ ማርቆስ የስብከተወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ፣ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የጉራጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ብፁዕ አቡነ ገብርኤል የምዕራብ ሸዋ ሀገረ ርብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ብፁዕ አቡነ በርተሎሜዎስ የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ብፁዕ አቡነ ኒቆዲሞስ የምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣የጠቅላይ ቤተክህነት የየምምሪያው ኃላፊዎች ተገኝተዋል።