የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን የ፲ ዓመት መሪ እቅድ ሥልጠና በብፁዕ ቅዱስ ፓትርያርኩ ቃለ በረከት ተከፈተ::

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት በመሪ እቅድ መምሪያ ያዘጋጀው የ፲ ዓመት መንፈሳዊና ዘላቂ የልማት ግቦች ጉባኤ በእግዚአብሔር ኃይል ጠንካራና ሁለገብ ኦርቶዶክሳዊ ማኅበረሰብን ለመገንባት እንተጋለን ! በሚል ርዕስ ለአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎችና ምክትል ሊቃነ መናብርት በተገኙበት በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ ሁለገብ አዳራሽ ዛሬ ሐሙስ ነሐሴ ፳፭ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም. ከጠዋቱ ፫ ሰዓት ጀምሮ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ውይይትና ምክክር እየተከናወነ ነው፡፡

በሰሜን አሜሪካ ተተኪ ካህናትን በበቂ ሁኔታ የማፍራት ሂደት ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) ገለጹ።

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በሰሜን አሜሪካን በሲራኪዮስ ከተማ በምትገኘው የገነተ ደናግል ቅድስት አርሴማ ወክርስቶስ ሰምራ ገዳም ተገኝተው በገዳሙ የአብነት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ለቆዩ አራት ተማሪዎች የዲቁና ማእረግ በመስጠት አባታዊ መመሪያን አስተላልፈዋል።

በቄለም ወለጋ ሀገረ ስብከት መዋቅራዊ አደረጃጀቱን የጠበቀ አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑን የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ገለጹ።

በአሁኑ ወቅት ሀገረ ስብከቱ በተረጋጋ መልኩ መዋቅራዊ አንድነቱን በማጠናከር ሥራውን እየሠራ ነው ያሉት ብፁዕነታቸው ከሀገር ሽማግሌዎች፣ ከምዕመናንና ከወጣቶች ጋር ባደረግናቸው ተደጋጋሚ ውይይቶች መዋቅራችንን በማስከበር ሥራዎቻችንን በሚገባ ማከናወን የምንችልበት ስልት ቀይሰን በመሥራት ላይ እንገኛለን፤ ሀገረ ስብከታችንም ፍጹም ሰላማዊና ሥራዎች በመግባባት የሚከናወኑበት ተቋም በመሆን ኃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል ብለዋል።

ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ዙሪያ የተላለፈ የሰላም መልዕክት፧

“ቀብጸት ነፍስየ ሰላመ ወረሳዕክዋ ለሠናይትየ፦ ነፍሴን ከሰላም አራቀ፣ በጎ ነገርን ረሳሁ” (ሰቆ ኤር. 33:17)

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዐሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤትና የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዚዳንት ፲፩ኛ ዓመት መታሰቢያ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በመካሔድ ላይ ይገኛል

የቅዱስነታቸው የሕይወት ታሪክ እንደሚከለው ይነበባል።

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ አምስትና በሕገ ቤተክርስቲያን አንቀጽ 19 ቁጥር 3 አስቸኳይ ጉዳይ ሲያጋጥም ምልዓተ ጉባኤ እንደሚያደርግ በተደነገገው መሠረት ሐምሌ 26ቀን 2015 ዓ.ም. ባካሄደው አስቸኳይ ምልዓተ ጉባኤ በቤተ ክርስቲያናችን ላይ በተፈጠረው ወቅታዊ የዶግማ፣ የቀኖናና የአስተዳደራዊ ጥሰቶችን አስመልክቶ ውሳኔዎች አሳልፏል፡፡