ቅድስት ልደታ ለማርያምና ደ.መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ አቀባበል መርሐ ግብር የተሳካ እንዲሆን ላደረገው አስተዋጽጾ ምጋና ተቸረ።

የቅዱስ ፓትርያርኩን ወደ አገራቸውና ወደ መንበረ ክብራቸው በሰላም መመለስን አስመልክቶ ለቤተ ክርስቲያናችንና ለቅዱስነታቸው ክብር በሚመጥን መልኩ የተዘጋጀው መርሐ ግብር የተሳካና ውጤታማ መሆን ይችል ዘንድ የማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታና የደብረ መድሐኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ ጽሕፈት ቤት ሊቃውንትና የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች ለመርሐ ግብሩ የሚመጥኑ ልዩልዩ ያሬዳዊ ዜማዎችን በማቅረብ በዓሉ በድምቀት እንዲከበር አድርገዋል።

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የአሜሪካ ሕክምናቸውን አጠናቀው ወደ አገራቸውና ወደ መንበረ ክብራቸው በሰላም ተመለሱ።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በሰሜን አሜሪካ ሲያደርጉት የቆዩትን ሕክምና አጠናቀው ዛሬ ማለዳ ወደ አገራቸውና ወደ ወንበረ ክብራቸው በሰላም ተመለሱ።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በሰሜን አሜሪካን የነበራቸውን ቆይታ በማጠናቀቅ ላይ ናቸው።

መስከረም 29 ቀን 2016 ዓመተ ምሕረት
“””””””””””””””””””””””””””””””””””””
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

ከነሐሴ 27 ቀን 2016 ዓመተ ምሕረት ጀምሮ በሰሜን አሜሪካን የሚገኙት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ቀደም ሲል በተያዘው የጉዞ መርሐ ግብር መሠረት ጥቅምት 1 ቀን 2016 ዓመተ ምህረት ወደ ኢትዮጵያ የሚመለሱ ይሆናል።
©የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት

የብፁዕ ወቅዱስ አባታችን በረከት አይለየን

የቦሌና ለሚ ኩራ ክፍላተ ከተሞች ቤተክህነት ጽሕፈት ቤት የ፳፻ ፲ወ፭ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ አደረገ፤ በሥራ አፈጻጸም ውጤት ያስመዘገቡ አድባራትን ሸለመ።

ዛሬ በቦሌና ለሚ ኩራ ክፍላተ ከተማ በተደረገ የ፳፻ ፲ወ፭ዓ.ም የሥራ አፈጻጸም ግምገማና የአዲሱ ዓመት ዕቅድ ዙሪያ በተደረገ ስብሰባ ላይ በክፍላተ ከተማው ሥር የሚሚገኙ አድባራትና ገዳማት በተለይም ውጤታማ የሥራ ክንውን ላደረጉት የሽልማት መርሐ ግብር ተከናውኗል።

ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል በመንገሺና ጎደሬ ወረዳዎች የተተከሉ ሦስት አብያተክርስቲያናትን ባርከው ቅዳሴ ቤታቸውን አክበሩ በቢሻን ዋዩ ሐርቅ ለሚተከለው የቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የመሰረት ድንጋይ አኖሩ።

ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል የጋምቤላና የደቡብ ሱዳን፣ የቤኒሻንጉል አሶሳ፣ቄለም ወለጋ ቤጊ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በጋምቤላ ሀገረስብከት መጃንግ ዞን መንገሺና ጎደሬ ወረዳዎች ለሐዋርያዊ አገልግሎት በመጓዝ ሦስት አዳዲስ የተሰሩ አብያተክርስቲያናትን በመባረክ ቅዳሴ ቤታቸውን አክብረዋል።

በኒው ዮርክና አካባቢው የሚገኙ የአሀት ኦርቶዶክሳዊት (Oriental) ቤተክርስቲያን ብፁዓን አበው፣ ካህናትና ምእመናን በጋራ ለጸሎተ ቅዳሴ ተሰባሰቡ።

የአሀት ኦርቶዶክሳውያን አብያተክርስቲያናት ብፁዓን አባቶች ጉባኤ ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ በኋላ የመጀመሪያ የሆነውን የጋራ የጸሎተ ቅዳሴ አገልግሎት መስከረም ፲፪ ቀን ፳፻፲፮ ዓ/ም በዌስት ኦሬንጅ ኒውጀርሲ በሚገኘው ደብረ ገነት ቅዱስ አማኑኤል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አከናውነዋል።

ማኅሌተ ጽጌ ወደ ፊንላንድኛ ቋንቋ ተተርጉሞ ተመረቀ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለማኅሌት አገልግሎት ከምትጠቀምባቸው መጻሕፍት መካከል አንዱ የሆነው የማኅሌተ ጽጌ መጽሐፍ ወደ ፊንላንድኛ ቋንቋ ተተርጎመ። ይህንን የአባ ጽጌ ድንግል ድርሰት የሆነው መጽሐፍ የተረጎሙት የፊንላንድ ሀገር ዜጋ የሆኑት እና ከሃምሳ ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ለአምስት ዓመታት ቆይታ ያደረጉት አቶ ኒሎ ሆንካነን ናቸው። ተርጓሚው መጽሐፉ ወደ ፊንላንድኛ ለመተርጎም ከ10 ዓመት በላይ ሲያጠኑ እንደቆዩና ዋና ምንጭ አድርገው የተጠቀሙት ደግሞ በ1919 ዓ.ም. በዶ/ር አዶልፍ ግሮህማን የተተረጎመውን የጀርመንኛ ቅጅ እንደሆነ ገልጸዋል።