የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

በኒው ዮርክና አካባቢው የሚገኙ የአሀት ኦርቶዶክሳዊት (Oriental) ቤተክርስቲያን ብፁዓን አበው፣ ካህናትና ምእመናን በጋራ ለጸሎተ ቅዳሴ ተሰባሰቡ።

October 4, 2023

መስከረም ፳፫ቀን ፳፻፲ ወ፮ዓ.ም
“””””””””””””””””””””””””””””””
የአሀት ኦርቶዶክሳውያን አብያተክርስቲያናት ብፁዓን አባቶች ጉባኤ ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ በኋላ የመጀመሪያ የሆነውን የጋራ የጸሎተ ቅዳሴ አገልግሎት መስከረም ፲፪ ቀን ፳፻፲፮ ዓ/ም በዌስት ኦሬንጅ ኒውጀርሲ በሚገኘው ደብረ ገነት ቅዱስ አማኑኤል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አከናውነዋል።

የጉባኤው አባላት በሆኑ ብፁዓን አባቶች ውሳኔ መሠረት የዘንድሮው ሥርዓተ ቅዳሴ እንዲመራ የታሰበው በብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ቢሆንም ብፁዕነታቸው በቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት በነበረባቸው ተደራራቢ ሥራ ምክንያት መገኘት ባለመቻላቸው በብፁዕነታቸው የተወከሉት መምህር አረጋዊ ሥርዓተ ቅዳሴውን በመምራት ተገቢውን መንፈሳዊ አገልግሎት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቀኖና መሠረት ተሰጥተዋል።

በሥርዓተ ቅዳሴው ላይም ከግብፅ፣ ከሕንድ፣ ከሶርያ፣ ከአርመንያና ከኤርትራ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት የመጡ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ ካህናትና ምእመናን ተገኝተዋል። ከቅዳሴው ባሻገርም በመጋቢት ወር ፳፻፲፭ ዓ/ም በጳጳሳት ጉባኤ በተወሰነው መሠረት አንድነትን ለማጠናከር በሚረዱ ጉዳዮች ላይ ጥልቅ ውይይት ተደርጓል።

ይህ የጳጳሳት ጉባኤ የሚያሳልፋቸው ጠቃሚ መንፈሳዊ ውሳኔዎች በሁሉም አሀት ኦርቶዶክሳውያን አብያተ ክርስቲያናት ተፈጻሚ እንዲሆኑ በብዙዎቹ አብያተ ክርቲያናት የታመነበት ሲሆን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንም የቅዱስ ሲኖዶስን የምልአተ ጉባኤ ውሳኔን እየጠበቀ መሆኑ ተገልጿል።

በጉባኤው ፍጻሜ ላይም የደብረ ገነት ቅዱስ አማኑኤል ቤተክርስቲያን ካህናትና ምእመናን በኢትዮጵያ ባሕላዊ ምግብና መስተንግዶ እንግዶችን አክብረዋል።
የአሀት ኦርቶዶክሳውያን አብያተ ክርስቲያናት ጉባኤውን በብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በአብያተ ክሮስቲያናትና በውጪ ግንኙነት ኀላፊነት እየመሩ ይገኛሉ።

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አዲስ የተሠራውን የለገዳዲ አንቀጸ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን መረቁ፡፡
  • የወጨ አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አዲሱ ሕንጻ በብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቦሌ ምዕራፈ ሰማዕታት ወደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የተከናወነው የወንዝ ማስቀየስ ሥራ ተጠናቆ በብፁዓን አባቶች ቡራኬ ተመረቀ።
  • በሸገር ሀገረ ስብከት የታነጸው የደብረ ሣህል ቅዱስ ገብርኤል አዲሱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ጸሎተ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሱማሌ ክልል ጅግጅጋ እና የምስራቅ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በምሥራቅ አርሲ አሰላ ከተማ ደብረ ምጽላል ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: ማኅሌተ ጽጌ ወደ ፊንላንድኛ ቋንቋ ተተርጉሞ ተመረቀ። Link to: ማኅሌተ ጽጌ ወደ ፊንላንድኛ ቋንቋ ተተርጉሞ ተመረቀ። ማኅሌተ ጽጌ ወደ ፊንላንድኛ ቋንቋ ተተርጉሞ ተ... Link to: ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል በመንገሺና ጎደሬ ወረዳዎች የተተከሉ ሦስት አብያተክርስቲያናትን ባርከው ቅዳሴ ቤታቸውን አክበሩ በቢሻን ዋዩ ሐርቅ ለሚተከለው የቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የመሰረት ድንጋይ አኖሩ። Link to: ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል በመንገሺና ጎደሬ ወረዳዎች የተተከሉ ሦስት አብያተክርስቲያናትን ባርከው ቅዳሴ ቤታቸውን አክበሩ በቢሻን ዋዩ ሐርቅ ለሚተከለው የቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የመሰረት ድንጋይ አኖሩ። ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል በመንገሺና ጎደሬ ወረዳዎች...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top