የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

ቅዱስ ሲኖዶስ የመጀመሪያ ቀን የዕለት ውሎ በአምስት አጀንዳዎች ላይ ውሳኔ መሰጠቱ ተገለጸ።

October 24, 2026
ጥቅምት 13 ቀን 2019 ዓ.ም
በፍትህ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቁጥር 164 እንደተደነገገው ቅዱስ ሲኖዶስ ጥቅምት 12 ቀን ምልአተ ጉባኤውን እንደሚያደርግ ይታወቃል። የ2019 ዓ/ም የጥቅምት ሲኖዶስ የመጀመሪያ ቀን የዕለት ውሎ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፤ መሪነት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ገዳም ጥቅምት 11ቀን 2019 ዓ.ም በጸሎት መጀመሩ ይታወሳል ።
ቅዱስ ሲኖዶስ በብፁዕ አቡነ ሉቃስ ሥርዓተ ቀብር ምክንያት ጥቅምት 12 ቀን 2019 ዓ.ም ስብሰባውን አራዝሞ ጥቅምት 12 ቀን በቅዱስ ፓትርያርኩ መክፈቻ ንግግር ጉባኤውን ጀምሯል ።
ቅዱስ ሲኖዶስ በቀዳሚው ቀን በአምስት አጀንዳዎች ላይ ውሳኔ መሰጠቱ ተገለጿል።
ለመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት EOTCTV መግለጫ የሰጡት በረዳት ፕሮፌሰር ዳንኤል ሰይፈሚካኤል የቅዱስ ሲኖዶስ ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ ምልዓተ ጉባኤው አጀንዳዎችን እንዲቀርጹ ሰባት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትን መሰየሙን ገልጸዋል ።
ምልዓተ ጉባኤው በተመረጡት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት አቅራቢነት ሃያ አምስት አጀንዳዎችን በማጽደቅ ጉባኤውን ማካሄድ መጀመሩን አሳውቀዋል ። የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በአጅንዳዎቹ ቅድም ተከተልም በአምስት አጀንዳዎች ላይም ውሳኔ አስተላልፏል ብለዋል።
ቅዱስ ሲኖዶስ በአጀንዳ አንድ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የመክፈቻ መልዕክትን የተመለከተ ሲሆን ፤ ቅዱስነታቸው ያስተላለፉት አባታዊ መልእክት ቅዱስ ሲኖዶስ በሁሉም አህጉረ ስብከት የቤተ ክርስቲያናችን የሥራ መመሪያ ሆኖ እንዲተገበር መወሰኑን በዕለታዊ መግለጫው ተገልጿል።
ቅዱስ ሲኖዶስ በሁለተኛው አጀንዳ የ45ኛው ዓለም አቀፍ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ስብሰባ የአቋም መግለጫን በተመለከተ፤ ውይይት ያደረገ ሲሆን ፤ ቃለ ጉባኤውና የአቋም መግለጫውን በመስማት፤ የአቋም መግለጫው የተወሰኑ ማስተካከያዎችን በማካተት ተግባራዊ እንዲሆን ለሁሉም አህጉረ ስብከት መመሪያ መስጠቱን በረዳት ፕሮፌሰር ዳንኤል ሰይፈሚካኤል ገልጸዋል ።
ቅዱስ ሲኖዶስ በቀጣይነት በሀገራዊ ሰላምና ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ችግሮችን በተመለከተ የተወያየ ሲሆን ፤ የሰላም ኮሚቴው ያከናወናቸው ጉዳዮች በዝርዝር ተመልክቷል ።
ቅዱስ ሲኖዶስ በሀገራችን በካህናት አገልጋዮችእና በምእመናን ላይ እየደረሰ ያለውን አጠቃላይ የሰላም ጉዳይ ትኩረት በማድረግ ውይይት አድርጓል። በዚህም ባለፈው ዓመት እና በዚሁ ዓመት በአርሲ እና አከባቢው እንዲሁም በሌሎችም በኦርቶዶክሳውያን ላይ የተፈፀመውን ግድያ እና መፈናቀል አውግዟል።
ችግሩ እንዲቀረፍም ከመንግሥት ጋር ውይይት እንዲደረግ መመሪያ እና አቅጣጫ መስጠቱ ተመልክቷል ።
ቅዱስ ሲኖዶስ በቀዳሚው ቀን ጉባኤው ከወላይታ ሀገረ ስብከት የቀረበውን ሥርዓተ ትምህርት በተመለከተ የተወያየ ሲሆን፤ ሥርዓተ ትምህርቱና ጥያቄው በሀገረ ስብከቱ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ቀርቦ፤ በቋሚ ሲኖዶስ ታይቶ፣ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የትምህርትና ማሠልጠኛ መምሪያ ታይቶና ተገምግሞ፤ በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ በአስቸኳይ ታይቶ ለውሳኔ እንዲቀርብ መደረጉ ታውቋል።
የካህናት ማሠልጠኛው አስፈላጊነት ታምኖበት በቀድሞው ፓትርያርክ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት (አባ መላኩ) ስም በአካባቢው ያለውን አሁናዊ ወይም ነባራዊ ግምት ውስጥ በማስገባት ማሰልጠኛው እንዲከፈት ውሳኔ መስጠቱን ለመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት EOTCTV መግለጫ የሰጡት በረዳት ፕሮፌሰር ዳንኤል ሰይፈሚካኤል አስታውቀዋል ።
©የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት/ EOTC Broadcasting Service Agency/
Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/pr2019.jpeg 336 418 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-10-24 05:01:092026-10-24 05:01:09ቅዱስ ሲኖዶስ የመጀመሪያ ቀን የዕለት ውሎ በአምስት አጀንዳዎች ላይ ውሳኔ መሰጠቱ ተገለጸ።
Search Search

Recent Posts

  • ቅዱስ ሲኖዶስ የመጀመሪያ ቀን የዕለት ውሎ በአምስት አጀንዳዎች ላይ ውሳኔ መሰጠቱ ተገለጸ።
  • መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ
  • የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ ከመላው አህጉረ ስብከት የሥራ ኃላፊዎች ጋር የምክክር መርሐ ግብር አካሄደ
  • የብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ የመዝጊያ መልዕክት
  • መልዕክተ ክቡር ም/ጠቅላይ ሚኒስትር

Archives

  • October 2026
  • September 2026
  • August 2026
  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church
  • Link to Facebook
Link to: መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ Link to: መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ
Scroll to top Scroll to top Scroll to top