የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎችን ውጤታማ ማድረግ የሚያስችል የድርጊት መርሐ ግብር ተዘጋጀ

***,******
ጥር ፳፩ ቀን ፲ወ፭ ዓ.ም
“”””””””””””””””””””””
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ

የሰ/ት ቤቶች አንድነት ኅብረት፣ ኦርቶዶክሳዊያን ሽማግሌዎች፣ የተለያዩ የማኅበራት ተወካዮች በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎች አተገባበር ላይ ከብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ጋር ተወያዩ።

የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎች ሁሉንም የቤተ ክርስቲያኗን አካላት ባሳተፈ መንገድ ውጤታማ እንዲሆኑም የድርጊት መርሐ ግብር ተቀርጿል ተብሏል።

ቅዱስ ሲኖዶስ በአስቸኳይ ምልዓተ ጉባኤው ጥር 14 በሕገ ወጥ መንገድ የተሾሙትን አካላት ማውገዙንና የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጆች፣ መንግስትና የተለያዩ አካላት ቤተ ክርስቲያንን እንዲጠብቁ ጥሪ ማቅረቡ ይታወቃል።