ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በመስቀል አደባባይ የሚከበረውን የደመራ በዓልን አስመልክቶ መልእክት አስተላለፉ።

መስከረም ፲፪ ቀን ፳፻፲ወ፮ ዓም
*****
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
“”””””””””””””””””””
ብፁዕነታቸው በመግቢያቸው ስለ ትግስት አስፈላጊነት እና ጠቀሜታ ትምህርት የሰጡ ሲሆን በበዓሉ ላይ የሚፈትኑ ጉዳዮች ሊገጥሙን ስለሚችሉ በትዕግስት ማለፍ አለብን ብለዋለል። በማስከተልም የዕለቱን መርሐ ግብር ያስተዋወቁ ሲሆን በይበልጥም ሰዓትን ማክበር ከፍተኛ ትኩረት እንደሚሰጠው አሳስበዋል። ብፁዕነታቸው የመግቢያ ባጅ እደላው በሕግና በሥርዓት ትኩረት ተሰጥቶት የሚከናወን መሆኑን ገልጸዋል።

ሰንደቅ ዓላማን በተመለከተም የፌዴራል እና የቤተ ክርስቲያን አርማ ብቻ ይለበት መሆን እንደሚገባውና ርችት መተኮስ የቤተ ክርስቲያን ሥርዐት ባለመሆኑ እንደማይፈቀድ ገልጸዋል። የቲሸርት አለባበስ በተመለከተም ተንኳሽ መልእክት መጠቀም አይገባም ያሉት ብፁዕነታቸው በየመንደሩና በየአጥቢያው በሚከበሩ በዓላት ላይም ጥንቃቄ ያስፈልጋል ብለዋል።
በበዓሉ ላይ የተፈቀደለት አስተናባሪ ብቻ የሚያስተናግድ ሲሆን ያልተፈቀደለት አካል ሲንቀሳቀስ ቢገኝ በወንጀል ያስጠይቃል ያሉት ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ መርሐ ግብር መሪዎች እና ተናጋሪዎች በተፈቀደላቸው ሰዓት እንዲጠቀሙ አሳስበዋል።።
በመጨረሻም ለመርሐ ግብሩ መሳካት ሁሉም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ አባታዊ ጥሪ አስተላልፈዋል። በዕለቱ የሙስሊም ወገኖቻችን የሚያከብሩት በዓል ስላላቸው በመከባበር እና በመተባበር በዓላቱን ማክበር ይገባል ሲሉም ጨምረው አሳስበዋል።
እንደዚሁ፦ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ዶ/ር የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የኒውዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በዓሉን አስመልክተው መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን ብፁዕነታቸው በበኩላቸው በዓሉ መንፈሳዊ ስለሆን በመንፈሳዊነት ልናከብረው ይገባል እንደዚሁም በታዛዥነት እና በእምነት በበዓሉ ላይ ልንታደም ይገባል ብለዋል።